1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኮቪድ ወርርሽኝ መከላከያ ክትባት እና ሥጋቱ 

ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 5 2014

ጀርመን ዉስጥ ከአንድ ወር በፊት የተከተበዉ የሕዝብ መጠን 67 በመቶ ነበር።  በቅርቡ የኮሮና ዝዉዉር ሕግ ጠበቅ እያለ መጥቶአል።  በማንኛዉም የሕዝብ መገልገያ የኮሮና መከላከያ ክትባትን ያልተከተበ ሰዉ ዉስጥ ገብቶ መገልገልና መገልገል እንደማይቻል ጠበቅ ያለ ቁጥጥር ከተጀመረ በኋላ የተከተበዉ ሰዉ ቁጥር አሁን ወደ 70 በመቶ ከፍ ብሎአል። 

https://p.dw.com/p/44GCf
Australien | Coronavirus | Melbourne
ምስል Robert Cianflone/Getty Images

ጀርመን ዉስጥ ከአንድ ወር በፊት የተከተበዉ የሕዝብ መጠን 67 በመቶ ነበር።  በቅርቡ የኮሮና ዝዉዉር ሕግ ጠበቅ እያለ መጥቶአል።  በማንኛዉም የሕዝብ መገልገያ የኮሮና መከላከያ ክትባትን ያልተከተበ ሰዉ ዉስጥ ገብቶ መገልገልና መገልገል እንደማይቻል ጠበቅ ያለ ቁጥጥር ከተጀመረ በኋላ የተከተበዉ ሰዉ ቁጥር አሁን ወደ 70 በመቶ ከፍ ብሎአል። 
የኢትዮጵያ ጉዳይ ስንመለከት በሃገሪቱ የኮሮና መከላከያ ክትባትን የወሰደዉ ሰዉ ቁጥር እዚህ ግባ የሚባል አይደለም። ላለመከተብ የሚሰጡ ምክንያቶች ወጣቶችን አይዝም፤ ከተረ ጉንፋን የሚል አይደለም፤ ሲይጣናዊ አምልኮ የሚከተሉ የበለፁ ሃገራት የሕዝብን ቁጥር ለመቀነስ ነዉ የሚሉ ምክንያቶች እና ሌሎችም እንደሚጠቀሱ ዶ/ር ቤዛ ወልዳረጋይ ለዶቼ ቬለ «DW» ተናግረዋል።  በተለይ ወጣቶች ከነዚህ አጉል አባባሎች ራሳቸዉን በማራቅ የመከላከያ ክትባቱን መዉሰድ እንዳለባቸዉ ባለሞያዎቹ አሳስበዋል። 

ዮሃንስ ገ/እግዚአብሔር 
አዜብ ታደሰ