1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኮቪድ 19 ወረርሽኝ በድሬደዋ

ሐሙስ፣ ሐምሌ 29 2013

ስርጭቱ እንደ አዲስ የመባባስ ምልክት እየታየበት የሚገኘውን የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ለመከላከል ኅብረተሰቡ ከመዘናጋት ወጥቶ ጥንቃቄ እንዲያደርግ የድሬደዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ አሳሰበ። ለበሽታው የሚሰጠው ክትባት እስካሁን ከጠቅላላው ነዋሪ ሦስት በመቶ ለሚሆነው ብቻ የመጀመርያው ዙር መሰጠቱም ገልጿል።

https://p.dw.com/p/3yaSg
Äthiopien Lemlem Bezabih

ጥንቃቄ ማድረግ እየተመከረ ነው

የድሬደዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ለምለም በዛብህ እንደ አዲስ ስርጭቱ እየተባባሰ መቷል ያሉት የኮሮና ተሐዋሲ ዓይነት ላይ ሀገር አቀፍ ጥናት እየተካሄደ መሆኑን ነው የሚናገሩት። ወረርሽኙ ተስፋፍቶ በብዙዎች ላይ የከፋ ጉዳት ከማድረሱ አስቀድሞም ኅብረተሰቡ እያሳየ ካለው መዘናጋት ወጥቶ ጥንቃቄ እንዲያደርግም አሳስበዋል፡፡

በአስተዳደሩ ዳግም በወረርሽኝ መልክ ሊከሰት ይችላል የሚል ስጋት ያለበትን የኮሮና ተሐዋሲ ለማከም ቀደም ሲል የነበሩ የህክምና ተቋማት ዝግጅትን የማሻሻል ሥራ ተሰርቷል ያሉት ኃላፊዋ ከሁሉ በፊት ግን  ቀድሞ ለመከላከል ሥራው ትኩረት ሊሰጥ እንደሚገባም አጽንኦት ሰጥተዋል። የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት በሀገሪቱ ሦስተኛው ዙር የኮቪድ 19 ወረርሽኝ እየጀመረ መሆኑን የሚያሳዩ ምልክቶች እየታዩ መሆናቸውን ከቀናት በፊት ገልጿል።

መሳይ ተክሉ

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ