የኮቪድ 19 ክትባት በብሪታንያ
ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 1 2013ማስታወቂያ
ብሪታንያ ከትናንት በስተያ ማክሰኞ አንስቶ የኮቪድ 19 ክትባትን ለዜጎቿ መስጠት ጀምራለች። ላለፉት 10 ወራት በተለይ በአውሮጳና በቀረው የዓለም ክፍል ከፍተኛ ስጋትና ሌላው ቀርቶ የመንቀሳቀስ ነፃነት ላይ ሳይቀር ጫና ያሳደረው የኮሮና ወረርሽኝ የተመራማሪዎችን አቅምና ዕውቀት ፈተና ውስጥ ከቷል። የተለያዩ ሃገራት የመድኃኒት አምራች ኩባንያዎች መከላከያ ክትባት እየቀመምን ነው ቢሉም በምዕራቡ ዓለም ተቀባይነት ያገኘው ፋይዘርና ባዮንቴክ የተባሉት ኩባንያዎች የደረሱበት ግኝት ነው። ለዚህ ምርምር ውጤት እውቅና የሰጠችው ብሪታንያ ክትቧቱን ለአዛውንት በመስጠት ብትጀምርም የጉሮሮ ህመምና የመተንፈስ ችግር ያስከተለባቸው እንዲሁም የሰውነት መቆጣት ያጋጠማቸው አሉ ተብሏል። ይህ በኅብረተሰቡ የመከተብ ፍላጎት ላይ ያሳደረው ነገር ይኖር ይሆን?
ድልነሳ ጌታነህን
ሸዋዬ ለገሠ
አዜብ ታደሰ