የኮቪድ-19 ሦስተኛ ማዕበል በአዲስ አበባ
ሰኞ፣ ነሐሴ 17 2013ማስታወቂያ
በኢትዮጵያ ሶስተኛ ዙር የኮሮና ተዋሲ ስርጭት ማዕበል ክስተት ለመስተዋሉ አመላካች ቁጥራዊ ሁኔታዎች መታየታቸው ተገለጸ፡፡
በተለይም በመዲናዋ አዲስ አበባ በተዋሲው ጦስ በፅኑ የሚታመሙ እና ህይወታቸው የሚያልፍ ሰዎች ቁጥር ባለፉት አራት ሳምንታት ከጤና ተቋሟቱ አቅም በላይ ሆኖ ተስተውሏል ብሏል የከተማ አስተዳደሩ ጤና ቢሮ፡፡
ወደ ኢትዮጵያ እየገባ ያለው የተዋሲው ክትባት ቁጥር ከፍ እያለ በመሆኑ በቅርቡ ከአንድ ሚሊየን የላቁ ዜጎችን በመዲናዋ ብቻ ለመከተብ እቅድ መያዙን የገለጹት የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዮሐንስ ጫላ ህብረተሰቡ ክትባቱን በየመንግስት ጤና ተቋማት በነጻ እንዲከተቡ አሳስበዋል፡፡
አስተያየታቸውን ለዶይቼ ቬለ የሰጡ የመዲናዋ ነዋሪዎች ግን ህብረተሰቡና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አሁንም የላላ ጥንቃቄ እንደሚያደርጉ ይናገራሉ፡፡
ስዩም ጌቱ
ሸዋዬ ለገሰ