1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኮሮናን ለመግታት የወጣ ገደብ ያስከተለዉ ፈተና  

ሰኞ፣ ሚያዝያ 12 2012

በኮሮና ወረርሽኝ ሳቢያ የአስቸኳያ ጊዜ አዋጅ በተደነገገባት ኢትዮጵያ የፋሲካ በዓል እንደ ወትሮውም ባይሆን  ቀዝቀዝ  ብሎ ተከብሯል። ከበዓሉ ቀደም ብሎ በዕለተ-አርብ እና ቅዳሜ የዋሉ የበዓል ገበያዎች ኢትዮጵያውያን ለኮሮና ተብሎ የታወጀውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ችላ ለማለታቸው ጠቋሚ ነበር።

https://p.dw.com/p/3bBMQ
Äthiopien Addis Abeba | Coronavirus | Kaffeehändlerin
ምስል DW/S. Muchie

ሻይና ዳቦ እየሸጠች ቤተሰብ የምታስተዳድረዋ ወይዘሮ ምሬት

በኮሮና ወረርሽኝ ሳቢያ የአስቸኳያ ጊዜ አዋጅ በተደነገገባት ኢትዮጵያ የፋሲካ በዓል እንደ ወትሮውም ባይሆን  ቀዝቀዝ  ብሎ ተከብሯል። ከበዓሉ ቀደም ብሎ በዕለተ-አርብ እና ቅዳሜ የዋሉ የበዓል ገበያዎች ኢትዮጵያውያን ለኮሮና ተብሎ የታወጀውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ችላ ለማለታቸው ጠቋሚ ነበር። የኮሮና ሥጋት እና ወረርሽኙን ለመከላከል የተጣሉ ገደቦች የበርካታ ኢትዮጵያውያንን ሕይወት አመሳቅለዋል። በተለይ ኑሮ ከእጅ ወደ አፍ ለሆነባቸው እንደ ወይዘሮ ሐድራ በድሩ ያሉ ዜጎች ገደቦቹ ሕይወትን የከፋ አድርጓል። ። በአዲስ አበባ ለቀን ሰራተኞች ሻይ፣ ዳቦ እና ብስኩት እየቸረቸሩ ኑሯቸውን የሚደግፉት ወይዘሮ ወረርሽኙ በሕይወታቸው ላይ ያሳደረውን ጫና ለዶይቼ ቬለ እንዲህ አስረድተዋል።

 

ሰለሞን ሙጬ

አዜብ ታደሰ

እሸቴ በቀለ