1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኮሮና ወረርሽኝን እየተከላከሉ መማር ይቻላል ተባለ

ማክሰኞ፣ መስከረም 12 2013

በኢትዮጵያ የኮሮና ወረርሽኝን እየተከላከሉ ትምህርት መጀመር የሚያስችሉ ቅድመ ሁኔታዎች መጠናቀቃቸውን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ። ሚኒስቴሩ እንዳለው በሀገሪቱ በሚገኙ ሁሉም ክልሎች የወረርሽኙ ተጨባጭ ሁኔታ እየተገመገመ የመማር ማስተማር ስራው በመስከረም መጨረሻ ይጀመራል።

https://p.dw.com/p/3iq1a
Äthiopien I Bildungsminister Getahun Mekuria
ምስል Yohannes Gebregziabher/DW

«የኮሮና ወረርሽኝን እየተከላከሉ ትምህርት መጀመር ይቻላል።»የትምሕርት ሚኒስቴር

በኢትዮጵያ የኮሮና ወረርሽኝን እየተከላከሉ ትምህርት መጀመር የሚያስችሉ ቅድመ ሁኔታዎች መጠናቀቃቸውን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ። ሚኒስቴሩ እንዳለው በሀገሪቱ በሚገኙ ሁሉም ክልሎች የወረርሽኙ ተጨባጭ ሁኔታ እየተገመገመ የመማር ማስተማር ስራው በመስከረም መጨረሻ ይጀመራል። በትምህርት ዘመኑ ሊሰጥ የታቀደው ትምህርቱ ባለፈውን የ2012 ዓ/ም በወረርሽኙ ስጋት የተስተጓጎለውን ማካካስ የሚቻልበት ሁኔታን ታሳቢ መደረጉን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከክልል የትምህርት ቢሮዎች ጋር ለሁለት ቀናት የሚቆይ ጉባዔውን ዛሬ በአዲስ አበባ በጀመረበት ወቅት ነው።

 


ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር


ታምራት ዲንሳ
እሸቴ በቀለ