1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኮሮና ክትባት ብሪታንያና የአውሮጳ ኅብረትን አወዛገበ

ሐሙስ፣ ጥር 20 2013

የአውሮጳ ኅብረት እና  በቅርቡ ከአውሮጳ ኅብረት የወጣችው ብሪታንያ በኮቪድ-19 ክትባት አቅርቦት በብርቱ እየተወዛገቡ ነው። የውዝግባቸው ሰበቡ ደግሞ፦ መቀመጫውን ብርታኒያ ያደረገው አስትራ ዜኒካ የትሰኘ የኮቪድ 19 የክትባት መድሃኒት አምራች ኩባንያ የተባለውን አላቀረበም በሚል ነው።

https://p.dw.com/p/3oXU8
Belgien Brüssel | Coronavirus | COVID-Boya, private Initiative
ምስል Johanna Geron/REUTERS

የኮቪድ ክትባት አውሮጳና ብሪታንያን አፋጧል

የአውሮጳ ኅብረት እና  በቅርቡ ከአውሮጳ ኅብረት የወጣችው ብሪታንያ በኮቪድ-19 ክትባት አቅርቦት በብርቱ እየተወዛገቡ ነው። የውዝግባቸው ሰበቡ ደግሞ፦ መቀመጫውን ብርታኒያ ያደረገው አስትራ ዜኒካ የትሰኘ የኮቪድ 19 የክትባት መድሃኒት አምራች ኩባንያ ከአውሮጳ ኅብረት ጋር በገባው ውል መሰረት በቂ የክትባት ብልቃጦችን ማቅረብ አልቻለም መባሉ ነው። ኅብረቱ ከኩባንያው ጋር ውል  የገባውና የቅድሚያ ክፍያ  የከፈለውም ለ400 ሚሊዮን የኮቪድ ክትባት ብልቃጦች እንዲቀርቡለት ነበር።  ኩባያው ግን ባለፈው አርብ በመጀምሪያው ዙር ሊያቀርብ የሚችለው 31 ሚሊዮን ብቻ መሆኑን መግለጹ የአውሮፓን የክትባት ዘመቻ አስተጓጉሏል። አፍሪቃውያን ክትባቱን በቅርቡ የማግኘታቸው ገና አጠያያቂ በሆነበት በአሁኑ ወቅት አውሮጳና ብሪታንያ እኔ ልቅደም እኔ ግብግብ ገብተዋል።  
የአውሮፓ ህብረት መቀመጫውን ብርታኒያ ካድረገው አስትራ ዜኒካ ከትሰኘ  የኮቪድ 19 የክትባት መድሀኒት አምራች ኩባንያ ጋር ከፍተኛ ጋር ውዝግብ ውስጥ ገብቷል። ህብረቱ ከኩባንያው ጋር ውል  የገባውና የቅድሚያ ክፍያ  የከፈለውም ለ400 ሚሊዮን የኮቪድ ክትባት ብልቃጦች ሲሆን ከነገ  ክትባቱ በአውሮፓ የመድሀኒት ኤጀንሲ በሥራ ላይ እንዲውል ከሚፈቀድበት ዕለት ጀምሮም 80 ሚሊዮን ብልቃጦችን በሚቀጥሉት ሁለት ወራት ለማቅረብ ነበር። ሆኖም ግን ኩባያው ባለፈው አርብ በመጀመሪያው ዙር ሊያቀርብ የሚችለው 31 ሚሊዮን ብቻ  መሆኑን መግለጹ የአውሮፓን የክትባት ዘመቻ አስተጓጉሏል። ከዚህ በተጨማሪም በአሁኑ ወቅት በሥራ ላይ ያለው የፒፋይዘር ባዮንቴክ ክትባት ኩባንያዎችም የምርት እጥረት ያጋጠመው መሆኑን የገለጸ ሲሆን፤ ይህም የአውሮፓ ህብረትን የክትባት መርሀ ግብር በተለይ ከአሜሪካና ብሪታኒያ ወደ ኋላ እንዲቀር አድርጎታል። አሜርካና ብሪታኒያ  እስካሁን የህባቸውን  10 ከመቶ  እንዳስከተቡ የተገለጸ ሲሆን የአውሮፓ ህብረት አገሮች ግን ገና 2 ከመቶ ብቻ እንደሆነ ነው  የሚነገረው።
የአውሮፓ ህብረት፣ የአስትራዜንካ ኩባንያን በውላቸው መሰረት ግዴታውን ይፈጽም ዘንድ ከፍተኛ ግፊት እያደረገ ነው። የኮሚሺኑ የጤና ኮሚሽነር ዶክተር ስቴላ ክሪያ ኪድስ የህብረቱ አገሮች ኩባንያው በውላቸው መሰረት ክትባቱን ማቅረብ ያለበት ስለመሆኑ አንድ አይነት አቋም ያላቸው መሆኑን በመግለጽ የመድሀኒትና ክትባት መድሀኒቶች ፋብሪካዎች በተለይ በዚህ የወረርሺኝ ወቅት ከፍተኛ ኃለፊነት ያለባቸው መሆኑ አስገንዝበዋል። 
ወረርሺኝ በተስፋፋበት ወቅት ላይ ነን። በርካታዎችን በሞት እያጣን ነው። ቁጥሩ ዝም ብሎ ቁጥር ወይም ስታትሲክስ አይድለም። እነዚህ ሰዎች ቤተሰቦች፣ ጉደኞችና፣የስራ ባልደረቦች ያሏቸው ናቸው። በመሆም የመድሀኒት ፋብሪካዎችና የክትባት አምራቾች ኩባንያዎች ቃላቸውን የመጠበቅ ሀላፊነት አለባቸው በማለት የመድሀኒትና ክትባቶች ገበያ እንደሌሎቹ ሸቀጦች ሳይሆን የሞትና የመዳን ጉዳይ መሆኑን አስገንዝበዋል።ድምጽ
የአስትራዜኒካ ኩባንያ ኃላፊዎች ግን ችግሩ የተፈጠረው ከብርታኒያ ውጭ ያሉት ፋብሪካዎች  በተፈለገው መጠን ማምረት ስላልቻሉ መሆኑን በመግለጽ፤ ስምምነታቸውን በማክበር ክትባቱን ለማቅረብ ጥረት እንደሚያደርጉ እያስታወቁ ነው ነው። ኩባንያው ብርታኒያ ካለው ትልቁ ፋብሪካው የሚያመረተውን ክትባት እዚያው ለብርታኒያ እንደሚያቀርብ የሚታወቅ ሲሆን፤ የአውሮፓ ህብረት ግን ከዚያም ቢሆን በውሉ መሰረት ለአውሮፓ አባል አገሮችም  ሊላክ ይገባል ባይ ነው። ኩባንያው  ግን  ከብሪታኒያ ጋር ውል የገባው  ከህብረቱ ቀደም ብሎ በመሆኑ  ቅድሚያ  የተሰጠውም  በዚህ ምክኒያት ነው ሲል ይከራከራል። 
የአውሮፓ ህብረት በበኩሉ ውላቸው የክትባቱ አስተማማኘነት በአውሮፓ የመድሀኒት ኤጀንሲ ሲረጋገጥ ወዲያውኑ እንዲያቀርብ እንጂ የቀዳሚና ተክታይ ጨዋታ የተካተተበት አይድለም በማለት የመከራከሪያ ሀሳቡን ውድቅ ያደርገዋል። የጤና  ኮሚሽነሯ ዶክተር ክይሪያኪድስ  የኩባንያው ክርክር ውኃ የማይቋጥርና እንዲህ ላለ የወረርሺኝ መከላከያ ክታባትም ሊጠቀስ እንደማይገባው ገልጠዋል።  «ክትባቱን ማቅረብ አለመቻል  የየተስማማንበትን ውል ማፈረስ ነው። መጀመሪያ የመጣ መጀመሪያ ይስተናገዳል የሚለው አመክንያ እዚህ አየሠራም። ይህ አመክንዮ ምናልብት ለስጋቤቶች ይሰራ እንደሆን እንጂ እንጂ ለእነደዚህ አይነቱ ቅድሚያ ለተከፈለበት ስምምነት አይለም» ብለዋል። 
የአውሮፓ ህብረት ባለስልጣኖች፤ የብርታኒያ መንግስት በአገሩ የሚመረተውን የክትባት ምርት ለራሱ ብቻ የሚያደርግ ከሆነ፤ ከአውሮፓም ለምሳሌ ከቤልጀምና ኔዘርላንድስ እየተመረቱ ወደ ብርታኒያ በሚላኩ የፒፋይዘርን ብዮንቴክ  ክትባቶች ላይ ህብረቱ ቁጥጥር ለማድረግ ሊገደድ ይችላል ሲሉ ተሰምተዋል።
ለተፈጠረው የክትባት እጥረት የህብረቱ አገሮች ምንም እንኳ የእንግሊዙን የክትባት አምራች ኩባንያ ተጠያቂ ቢያደርጉም እጅግ አንገብጋቢ ለሆነው የክትባት ፕሮግርም መጓተት ግን ኮሚሽኑን ተጠያቂ እያደረጉ ነው። አንዳንዶች እንደውም ህብረቱ እውቅና ካልሰጣቸው የክትባት አምራች ኩባያዎች  ጋር ስምምነት ለማድረግ እያሰቡ መሆኑን እየገለጹ ነው። ይህ የኮቭድ ክትባት ሺሚያና ሺኩቻ ህብረቱን  በቅርቡ ከተለይችው ብርታኒያ ጋር ያለውን ግንኑነት እንድያሻክረው ያሰጋ ሲሆን፤ በአጠቃላይ ግን  የክትባቱ ምርት እጠረትና የባለጸጋዎቹ አገሮች ሺሚያ በአገሮች መካከል ያለውን ግንኑነትም እያሻከረው መሆኑን የሚያሳይ ብቻ ሳይሆን፤ የድሀ አገሮች ክትባቱን የሚያገኙበት ግዜ መቼ እንደሚሆን መገመት የሚያስቸግር መሆኑንም የሚያመላክት ሁኗል። 

Brüssel I EU I Ursula von der Leyen
ምስል Francois Walschaerts/REUTERS
Deutschland Riesa | Coronavirus, Impfzentrum
ምስል Maja Hitij/Getty Images


ገበያው ንጉሴ

አዜብ ታደሰ

ማንተጋፍቶት ስለሺ