1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኮሮና ክትባት በቅርቡ መሰጠት ይጀምራል ተባለ

ሰኞ፣ የካቲት 29 2013

ትናንት አዲስ አበባ የገባው 2.2 ሚሊዮን የአስትራ ዜኒካ የኮቪድ - 19 ክትባት ከዚህ ሳምንት ጀምሮ በፍትሓዊነትና ግልፅነት የክትባቱ አሰጣጥ መርሆዎች መሰረት ጥቅም ላይ መዋል ይጀምራል ተባለ።

https://p.dw.com/p/3qMM5
Äthiopien | AstraZeneca | COVAX-Impfstoff
ምስል Amanuel Sileshi/AFP

ትናንት አዲስ አበባ የገባው 2.2 ሚሊዮን የአስትራ ዜኒካ የኮቪድ - 19 ክትባት በቅርቡ በፍትሓዊነትና ግልፅነት የክትባቱ አሰጣጥ መርሆዎች መሰረት ጥቅም ላይ መዋል ይጀምራል ተባለ።የጤና ሚኒስቴር ዛሬ ለ ዶይቼ ቬለ ( DW ) እንዳስታወቀው ክትባቱ ቅድሚያ ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች እንደየ ተጋላጭነት ደረጃቸው የሚዳረስ ሆኖ በሁሉም ክልሎች በሚገኙ የጤና ተቋማት ይሰጣል። በተጨማሪም ለመንቀሳቀስ ችግር ላለባቸው በህመም እና በእርጅና ውስጥ ለሚገኙ ዜጎች ተንቀሳቃሽ ክትባት ሰጪ ግብረኃይል ክትባቱን እንደሚሰጥ ተገልጿል።

ሰለሞን ሙጬ
ልደት አበበ
አዜብ ታደሰ