1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኮሮና ኤኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ተጽእኖዎች 

ሰኞ፣ መጋቢት 28 2012

ዶቼቬለ ያነጋገራቸው በሃዋሳ ዩኒቨርስቲ የኤኮኖሚ መምህር ዶክተር ዶክተር ደገላ ኢርገኑ በሽታው ከሚያስከትለው የህክምና ቀውስ በላይ ኤኮኖሚያዊ ጉዳቱ ያመዝናል ብለዋል።የህክምና ባለሞያው ዶክተር ሲሳይ ለማ ደግሞ  በህክምናው ላይ ድርብ ጉዳት የሚያሳድረው ኮሮና የሚያስከትለው ማህበራዊ ቀውስ ቀላል  እንደማይሆን ገልጸዋል።

https://p.dw.com/p/3aYQU
Griechenland Corona-Pandemie Flüchtlingslager
ምስል DW/F. Campana

የኮሮና ተህዋሲ ወረርሽኝ ኢትዮጵያን ጨምሮ በአፍሪቃ ሃገራት ልዩ ልዩ ኤኮኖሚያ እና ማህበራዊ ጫናዎች ሊያስከትል እንደሚችል ምሁራን ተናገሩ።በጉዳዩ ላይ ዶቼቬለ ያነጋገራቸው በሃዋሳ ዩኒቨርስቲ የኤኮኖሚ መምህር ዶክተር ዶክተር ደገላ ኢርገኑ በሽታው ከሚያስከትለው የህክምና ቀውስ በላይ ኤኮኖሚያዊ ጉዳቱ ያመዝናል ብለዋል።የወጭና ገቢ ንግድን ያዳከመው ኮሮና ኢትዮጵያን በመሳሰሉ ሃገራት ከባድ የፈተና ዓመታትን ሊያስከትል እንደሚችልም ተናግረዋል።የህክምና ባለሞያው ዶክተር ሲሳይ ለማ ደግሞ  በህክምናው ላይ ድርብ ጉዳት የሚያሳድረው ኮሮና የሚያስከትለው ማህበራዊ ቀውስ ቀላል  እንደማይሆን ገልጸዋል።የአዲስ አበባው ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ዝርዝሩን ልኮልናል።


ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ