1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኮሮና ተፅዕኖ በምሥራቅ አፍሪካ አገራት ኤኮኖሚ

ረቡዕ፣ ግንቦት 12 2012

በምሥራቅ አፍሪካ አገራት በኮሮና የተያዙ ሰዎች ቁጥር ቀስ በቀስ እየጨመረ ሥጋቱም እያየለ ነው።ምዕራባውያን ምጣኔ ሐብታቸው እንዲያገግም ደፋ ቀና ማለት ሲጀምሩ ወረርሽኙ ኢትዮጵያ እና ኬንያን በመሳሰሉ አገራት የሚሰራጭበት ፍጥነት መረጋጋት አላሳየም። ለመሆኑ በአፍሪካ ቀንድ አገራት ኤኮኖሚ የኮሮና ተፅዕኖ ምን ያክል ይከፋል?

https://p.dw.com/p/3cY93
Bildergalerie Kulturelle Gesichtsbedeckungen - Kenia
ምስል picture-alliance/ZumaPress/D. Odhiambo

ከአቶ ቴዎድሮስ ሲሳይ ጋር በኮሮና ኤኮኖሚያዊ ጫና ላይ የተደረገ ቃለ መጠይቅ

የኮሮና ወረርሽኝ ባሳደረው ተፅዕኖ ሳቢያ ለ2.2 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን የሥራ ዕድል የፈጠረው የቱሪዝም ዘርፍ አደጋ ውስጥ ገብቷል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከጥር እስከ ሚያዝያ ባሉት አራት ወራት ውስጥ ብቻ 550 ሚሊዮን ዶላር አጥቷል። በጎርጎሮሳዊው 2020 ዓ.ም. ለኢትዮጵያ 400 ሚሊዮን ዶላር ያስገኛል ተብሎ ይጠበቅ የነበረው የአበባ ንግድ በዚሁ ዓለም አቀፍ ወረርሽኝ ለኪሳራ ከተጋለጡ መካከል ይገኝበታል። ይኸ ግን የኢትዮጵያ ኤኮኖሚ ብቻውን የገጠመው ቀውስ አይደለም። ታንዛኒያ፣ ኬንያ እና ዩጋንዳን የመሳሰሉ የምሥራቅ አፍሪካ አገራት ገበያዎች ከኢትዮጵያ የሚመሳሰል ፈተና ገጥሟቸዋል።

ዴሎይት የተሰኘው ኩባንያ ወረርሽኙ በክፍለ አህጉሩ ላይ የሚያሳድረውን ተፅዕኖ የሚዳስስ ሰነድ ይፋ አድርጓል። በዛሬው የከኤኮኖሚው ዓለም መሰናዶ እሸቴ በቀለ ሰነዱን ካዘጋጁ ባለሙያዎች መካከል አንዱ የሆኑት አቶ ቴዎድሮስ ሲሳይን አነጋግሯል። አቶ ቴዎድሮስ ሲሳይ በዴሎይት ኩባንያ የምስራቅ አፍሪቃ ቢሮ ተባባሪ ዳይሬክተር እና የፋይናንስ አማካሪ ናቸው። 

ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ የድምፅ ማዕቀፉን ይጫኑ

እሸቴ በቀለ