1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኮሮና ስርጭት በኢትዮጵያ 

ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 26 2013

በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱ ተደጋግሞ እየተነገረ ነው። የሟቾች ቁጥርም ቢሆን ከወትሮው በተለየ ሁኔታ እያሻቀበ በሽታውም የጤና ሥጋት ሆኖ መቀጠሉ እየተነገረ ነው። 

https://p.dw.com/p/3sxUf
BG "Die Welt im Griff von Corona"
ምስል Rodger Bosch/AFP/Getty Images

ሕብረተሰቡ የጥንቃቄ መቀዛቀዝ ይታይበታል

በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱ ተደጋግሞ እየተነገረ ነው። የሟቾች ቁጥርም ቢሆን ከወትሮው በተለየ ሁኔታ እያሻቀበ በሽታውም የጤና ሥጋት ሆኖ መቀጠሉ እየተነገረ ነው።  በሌላ በኩል ሕብረተሰቡ የሚያደርገው ጥንቃቄ መቀዛቀዝ ይታይበታል።
የሆስፒታሎች በታማሚዎች መሞላት፣ የኦክስጅንና የመተንፈሻ መሣሪያ እጥረት ዋና ዋና ችግር ከሆኑ ቆይተዋል። ከተፈጠረባቸው ሥጋት አንፃር በኮቪድ ህክምና ማዕከላት ውስጥ የሚሰሩ ባለሙያዎች በማዕከላቱ እየሰሩ ነገር ግን የቤተሰቦቻቸውን ጭንቀት ለመቀነስ ትክክለኛ የሥራ ቦታቸውን እንደማይናገሩ ለማወቅ ተችላል። የዛሬው የጤና ዝግጅት በዚሁ እየተስፋፋ በመጣው የኮሮና ወረርሽኝ አሁናዊ ሁኔታና እየተከናወኑ ስላሉ የመከላከል ጥረቶች ላይ ያተኮረ ነው።

ሰለሞን ሙጬ
አዜብ ታደሰ