የካታሎንያ ፖለቲከኞች ያለመከሰስ መብት ለማንሳት የተላለፈው ውሳኔ
ማክሰኞ፣ መጋቢት 7 2013ማስታወቂያ
ባለፈው ሳምንት የአውሮፓ ምክር ቤት ሶስት የስፔን ካታላን ግዛት የምክር ቤት አባላትን ያለመከሰስ መብት አንስቷል። ውሳኔው የተላለፈባቸው ፖለቲከኞች ከሶስት አመታት ገደማ በፊት በካታላን ግዛት በተካሔደው ሕዝበ-ውሳኔ በነበራቸው ሚና በስፔን መንግሥት የተከሰሱ ናቸው። የካታሎንያ ግዛትን እጣ-ፈንታን ለመወሰን የተካሔደው ሕዝበ-ውሳኔ አስቀድሞ በስፔን ሕገ-መንግሥታዊ ፍርድ ቤት ሕገ-ወጥ ተብሎ ነበር። በዛሬው የአውሮፓ እና ጀርመን መሰናዶ ገበያው ንጉሴ የአውሮፓ ምክር ቤት ያሳለፈውን ውሳኔ ይመለከታል።
ገበያው ንጉሴ
እሸቴ በቀለ