1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የካሜሩን ዉዝግብና ከታንዛንያ የብሩንዲ ተመላሽ ስደተኞች 

ቅዳሜ፣ መስከረም 24 2012

ትኩረት በአፍሪቃ በዚህ ሳምንት ያተኮረው በሁለት የአፍሪቃ አገሮች ላይ ነው። አንደኛው በታንዛኒያ ተገን ጠይቀዉ በሚኖሩት የብሩንዲ ስደተኞች ሁኔታ ላይ ነው። ስደተኞቹ ቁጥራቸው በአሥርና በሃምሣ ሺህ፣በመቶና ሁለት መቶ ሺህ ይቆጠራል። በሁለተኛነት የያዘዉ ርዕሰ ጉዳያችን ደግሞ ችግር አላጣ ባለዉ በካሜሩን ላይ ያተኩራል ።

https://p.dw.com/p/3Qlx0
Burundische Flüchtlinge fliehen vor Gewalt und den politischen Spannungen Burundis nach Tansania
ምስል AP/J. Delay

ትኩረት በአፍሪቃ


ትኩረት በአፍሪቃ በዚህ ሳምንት ያተኮረው በሁለት የአፍሪቃ አገሮች ላይ ነው። አንደኛው በታንዛኒያ ተገን ጠይቀዉ በሚኖሩት የብሩንዲ ስደተኞች ሁኔታ ላይ ነው። ስደተኞቹ ቁጥራቸው በአሥርና በሃምሣ ሺህ፣በመቶና ሁለት መቶ ሺህ ይቆጠራል። ወደ አንድ ሺህ የሚጠጉ የብሩንዲ ስደተኞች በሚቀጥለው ሳምንት ሐሙስ ተገን ከጠየቁበት ከታንዛኒያ  ወደ አገራቸው ይመለሳሉ ተብሎ እዚያ ይጠበቃል። በሌላ በኩል "ሁኔታው በብሩንዲ አልተቀየረም፣ ስለዚህ አንመለስም " የሚሉ የስደተኞች ድምፅ ተሰምቶአል።ታንዛኒያ ቢቆዩ መከራ፣ ወደ ወደ አገራቸው ቢመለሱ ፣እንደዚሁ መከራ ስለሆነባቸው የብሩንዲ ስደተኞች ጉዳይ  የእለቱ ትኩረት በአፍሪቃ የሚዳስሰዉ ርዕሰ ጉዳይ ነዉ። 
በሁለተኛነት የያዘዉ ርዕሰ ጉዳያችን ደግሞ ችግር አላጣ ባለዉ በካሜሩን ላይ ያተኩራል ። እዚያም "የእንግሊዘኛ ቋንቋ ተናጋሪዎቹ ፣ከፈረንሣዮቹ ተገንጥለው ፣የአገሪቱን አንድነት አፍርሰው የእራሳቸውን መንግሥት፣የአምባሶንያን ግዛት አቋቁመዋል።" የአፍሪቃ አንድነት ማህበረሰብና እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቻርተር ይህን እርምጃ ''... ይቀበሉት ፣ወይም ያውግዙት '' እራሱን የቻለ አርእስትና የሕግ ጥያቄ ሆንዋል። እንድያም ሆኖ በሚቀጥለዉ ሳምንት የካሜሩኑ ፕሬዚዳንት ፓል ቢያ የጠሩትን "ብሔራዊ የክብ ጠረጴዛ ውይይት ''  መሠረት ያደረገ  ዘገባም ይዘናል።  የካሜሩን ችግር የብዙ አፍሪቃ መንግሥታት ችግር ነው። ካሜሩን አሁን የያዘዘችው መፍትሔ ደግሞ  አማራጭ የሌለው ነው። በጥቂት ቀናት ስብሰባ አንዳች ነገር ላይ ደርሳለን ብሎ መገመት ግን ከባድ ነው። ''ፓለቲካ ''አንዴ የጀርመኑ ምሁር ማክስ ቬበር እንደለው "... ጠንካራ ጣውላን ቀስ ብሎ በመሮ እንደ መሰርሰር ዓይነት ነው።" 


ይልማ ኃይለሚካኤል
አዜብ ታደሰ