1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የካማሺ ዞን ተፈናቃዩች አቤቱታ

ማክሰኞ፣ ግንቦት 9 2014

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካማሺ ዞን በሎጅጋንፎይ (ምዥጋ) የተባለ ወረዳ የሚገኙ ተፈናቃዩች ሰብአዊ ዕርዳታ እየደረሳቸው እንዳልሆነ ተናገሩ፡፡ ከመጋቢት ወር ወዲህ ሰብአዊ ድጋፍ እንዳልደረሳቸው የተናገሩት ነዋሪዎቹ ሰብአዊ ድጋፍ ለማዳረስ በተቋቋሙ ኮሚቴዎች በኩል እርዳታው ላልተፈለገ ዓላማ እየዋለ ነው ይላሉ።

https://p.dw.com/p/4BMRu
Grenze zwischen Äthiopien und Sudan
ምስል Negassa Dessalegn/DW

የዞኑ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር በበኩሉ «ሰብአዊ እርዳታ ላልተፈለገ ዓላማ ውሏል የተባለውን ክስ ተጨባጭ ያልሆነ እና ያልተረጋገጠ አሉባልታ ነው» ሲሉ ለDW  አብራርተዋል፡፡ አቅርቦቱን በተመለከተ ለዞኑ የደረሰው ሰብአዊ ድጋፍ አነስተኛ እንደነበረ የዞኑ አደጋ ስራ አመራር ተወካይ አቶ ተመስገን ኢተፋ አክለዋል፡፡ የአሶሳው ወኪላችን ነጋሳ ደሳለኝ ተጨማሪ አለው።

በካማሺ ዞን በሎጅጋንፎይ ወረዳ  በገጠራማ መንደሮች ውስጥ ባለፈው ዓመት በነበረው የጸጥታ ችግር ምክንያት ተፈናቅለው  ሶጌ በሚትባል የወረዳው ከተማው እንደሚገኙ  የነገሩን  ነዋሪ ለ2 ወራት ያህል እርዳታ  እንዳልተደረሳቸው  ተናግረዋል፡፡ ለተፈናቀሉ ዜጎች የተላኩ የሰብአዊ ዕርዳታዎች ለድጋፍ ፈላጊ ማህበረሰብ በአግባቡ እየደረሰ እንዳልሆነ የገለጹት በሶጌ ከተማ የሚገኙት አቶ አባቡ ጉኢ በሚያዚያና መጋቢት ወር ድጋፍ እንዳላገኙ አብራርተዋል፡፡ ከዜጎች ድጋፍ በእጀባም ወደ ስፍራው ቢደረስም ድጋፍ ለማዳረስ የተቋቋሙ ኮሚቴዎች ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ባለመወጣቸውና ላልተፈለገ ዓላማ በማዋላቸው የድጋፍ እጥረት እንዳጋጠማቸው ጠቁመዋል፡፡

የካማሺ ዞን ኮሙኒኬሽን መምሪያ የኮሙኒኬሽን ባለሙያ የሆኑት አቶ ጀርሞሳ ተገኘ ለDW በሰጡት ማብራሪያ በዞኑ እንደ አጠቃላይ የቀረበው  የሰብአዊ ድጋፍ  አነስተኛ መሆኑን ገልጸው በበሉ ጅግጋንፊይ ወረዳ የተፈናቀሉ ዜጎች ቅሬታ እንደቀረበ አመልክተዋል፡፡ ሚያዚያ 22/2014 ዓ፣ም  ወደ ወረዳው የቀረበው ድጋፍ ለተፈናቀሉ ዜጎች በአግባቡ እንዳልደረሰ ከሰዎች ጥቆማ መቅረቡንና ጉዳዩም እየተጣራ እንደሚገኝ አብራርተዋል፡፡

የካማሺ ዞን የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ተወካይ አቶ ተመስጌን  ኢተፍ በዞኑ ሶስት ወረዳዎች ውስጥ ለሚገኙ የተፈናቀሉ ዜጎች ድጋፍ መሰራጨቱን አስታውቋል፡፡ ሰብአዊ ድጋፍ  አስመክልቶ የቀረቡ ቅሬታዎችን የተረጋገጡ መረጃዎች እንዳልሆኑና  ለቢሮአቸው የደረሰ ጥቆማ እደለለ ገልጸዋል፡፡.

በካማሺ ዞን ከ100ሺ በላይ ዜጎች በመጠለያ ጣቢያ ውስጥ እንደሚገኙ የዞኑ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ገልጸዋል፡፡ በሎ ጅጋፍይ የተባለ ወረዳ ውስጥ ብቻ 46ሺ  የሚደርሱ የተፈናቀሉ ዜጎች በወረዳው ከተማ እንደሚገኙ የዞኑ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ተወካይ አቶ ተመስጌን ኢተፋ ተናግረዋል፡፡

ነጋሳ ደሳለኝ

ልደት አበበ
ኂሩት መለሠ