1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኦብነግ መግለጫ

ረቡዕ፣ ነሐሴ 15 2011

የግንባሩ የሥራ ሃላፊዎች ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ በሰጡት መግለጫ ምርጫው በተያዘለት ጊዜ መካሄድ እንዳለበትም አሳስበዋል። ምርጫው ፍትሀዊ ሀቀኛ እና ለሰላም የሚበጅ ይሆናል ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉም  ተናግረዋል። ግንባሩ የተጀመረውን ለውጥ ለማስቀጠል ከኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ጎን በመቆም የበኩሉን ድርሻ እንደሚወጣም አስታውቋል።

https://p.dw.com/p/3OHSg
Äthiopien Ogaden National Liberation Front PK
ምስል DW/Y. Geberegziabeher

የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻ አውጭ ግንባር መግለጫ


የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻ አውጭ ግንባር በምህጻሩ ኦብነግ በመጪው ዓመት በሚካሄደው የኢትዮጵያ አጠቃላይ ምርጫ እንደሚሳተፍ አስታወቀ። የግንባሩ የሥራ ሃላፊዎች ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ በሰጡት መግለጫ ምርጫው በተያዘለት ጊዜ መካሄድ እንዳለበትም አሳስበዋል። ምርጫው ፍትሀዊ ሀቀኛ እና ለሰላም የሚበጅ ይሆናል ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉም  ተናግረዋል። ግንባሩ የተጀመረውን ለውጥ ለማስቀጠል ከኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ጎን በመቆም የበኩሉን ድርሻ እንደሚወጣም በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ ተገልጿል። ጋዜጣዊ መግለጫውን የተከታተለው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ዝርዝሩን ልኮልናል።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ