የኦነግ ሠራዊት አባላት እየተመለሱ ነው
ሐሙስ፣ የካቲት 14 2011ማስታወቂያ
የኦሮምያ ክላላዊ መንግሥት የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ኦነግ ከዚህ ቀደም በደረሱበት ስምምነት መሠረት ካለፉት 3 ቀናት አንስቶ የኦነግ ሠራዊት አባላት ወደ ተለያዩ ጊዜያዊ ካምፖች እየገቡ ነው። አቀባበልም እየተደረገላቸው ነው። እስካሁን ግን አሉ ከተባሉት የሠራዊት አባላት ግማሽ ያህሉ እንኳን አልተመለሱም ተብሏል። ምንም እንኳን በማህበራዊ መገናኛ ብዙሀን ትጥቅ አንፈታም ያሉ የኦነግ ሠራዊት አባላት አሉ ተብሎ በማህበራዊ መገናኛ ብዙሀን ቢሰራጭም DW ያነጋገራቸው አባገዳ ግን ትጥቅ አልፈታም ያለ አካል የለም ሲሉ መልሰዋል። ስለ ሂደቱ የአሶሳውን ዘጋቢያችንን ነጋሳ ደሳለኝን በስልክ አነጋግሬዋለሁ።
ነጋሳ ደሳለኝ
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ