1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር መንግስትን መክሰሱ

ሰኞ፣ ጥር 25 2012

ሰዎች በጅምላ ይታሰራሉ፣ የሰብአዊ መብት ረገጣም እየደረሰ ነው የሚለው ግንባሩ ፣ ክስተቱ ሆን ተብሎ በመንግስት እየተፈጸመ ያለ ነውም ብሏል። የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሳያውጅ የተሰማሩ የኮማንድ ፓስት አባላት ለአንድ አመት ህዝቡን እያስጨነቁ በመሆኑ ወደ ካምፓቸው እንዲመለሱ የግንባሩ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ቀጀላ መርዳሳ ጠይቀዋል።

https://p.dw.com/p/3XDZ1
Kejela Megersa
ምስል DW/S. Getachew

ኦነግ መንግስትን ከሰሰ

በደቡባዊ ኦሮሚያ ዞኖች እና በምዕራብና ቄለም ወለጋ አካባቢዎች የመንግስት ወታደሮች በንጹሃን ዜጎች ላይ ግድያ እየፈጸሙ ነው ሲል የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ኦነግ ከሰሰ።
ሰዎች በጅምላ ይታሰራሉ፣ የሰብአዊ መብት ረገጣም እየደረሰ ነው የሚለው ግንባሩ ፣ ክስተቱ ሆን ተብሎ በመንግስት እየተፈጸመ ያለ ነውም ብሏል።
በተጠቀሱት አካባቢዎች ይህን ድርጊት እየፈጸሙ ያሉት ወታደሮች የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሳያውጅ የተሰማሩ የኮማንድ ፓስት አባላት ሲሆኑ ለአንድ አመት ህዝቡን እያስጨነቁ በመሆኑ ወደ ካምፓቸው እንዲመለሱ መቸየቃቸውን የግንባሩ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ቀጀላ መርዳሳ ለዶቼ ቬለ ( DW ) ተናግረዋል።
በዜጎች ላይ ደርሷል ያለውን ጉዳትም ገለልተኛ እና ነጻ አካል እንዲመረምረው በማለት ግንባሩ ጠይቋል። 

ሠለሞን ሙጬ

ታምራት ዲንሳ
 
አዜብ ታደሰ