1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኦሮሞ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ወቀሳና የገዢዉ ፓርቲ መልስ

ሐሙስ፣ የካቲት 25 2013

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) እና የኦሮሞ ፌደራዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) በተደጋጋሚ ግን በየፊናቸዉ እንደሚወቅሱት ገዢዉ ፓርቲ መሪዎቻቸዉን ሳይቀር አስሯል፣በየአካባቢዉ የሚገኙ ፅሕፈት ቤቶቻቸዉን ዘግቷል።ኦፌኮ «ተገፋሁ» በሚል በምርጫዉ እንደማይሳተፍ ትናንት አስታዉቋል።

https://p.dw.com/p/3qDbD
Ethiopia, Addis Abeba | Oromia PP reaction on OFC withdrawal from the coming election
ምስል Seyoum Getu/DW

የኦሞ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ወቀሳና የብልፅግና መልስ

በኦሮሚያ ክልል የሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች  በመጪው ግንቦት ሊደረግ በታቀደው ምርጫ እንዳይሳተፉ ገዢዉ የብልፅግና ፓርቲ «ጫናና ግፊት» ያደርግብናል በማለት የሚያቀርቡትን ወቀሳ አንድ የገዢዉ ፓርቲ ባለስልጣን አስተባበሉ።የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) እና የኦሮሞ ፌደራዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) በተደጋጋሚ ግን በየፊናቸዉ እንደሚወቅሱት ዢዉ ፓርቲ መሪዎቻቸዉን ሳይቀር አስሯል፣በየአካባቢዉ የሚገኙ ፅሕፈት ቤቶቻቸዉን ዘግቷል።ኦፌኮ «ተገፋሁ» በሚል በምርጫዉ እንደማይሳተፍ ትናንት አስታዉቋልም።የብልፅግና ፓርቲ የኦሮሚያ ቅርንጫፍ ፅሕፈት ቤት ኃላፊ ታዬ ደንደዓ ለዶቸ ቬለ በሰጡት መግለጫ ግን ትችት ወቀሳዉን አጣጥለዉ ነቅፈዉታል።አቶ ታዬ እንደሚሉት ፓርቲያቸዉ መጪዉን ምርጫ ነጻና ዴሞክራሲያዊ ለማድረግ እየሰራ ነው፡፡

ስዩም ጌቱ

ነጋሽ መሐመድ

ማንተጋፍቶት ስለሺ