1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኦሮሚያ መንግሥት ከመከላከያ ጎን ለመሰለፍ መዘጋጀቱ

ዓርብ፣ ሐምሌ 9 2013

የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስትና ሕዝብ የሀገር ሉዓላዊነት ጋሻ ከሆነው የመከላከያ ሠራዊት ጎን በመሆን መስዋእትነት ለመክፈል ዝግጁ ነው ያለው መግለጫው ለክልሉ ማህበረሰብም የድጋፍ ጥሪ አቅርቧል።መግለጫው ህዋሓትን በህዝቦች መሀከል ቁርሾና ክፍፍል በመፍጠር እንዲሁም የአገር ፍቅር እንዲሸረሸር በማድረግ ኮንኗል።

https://p.dw.com/p/3waad
Karte Äthiopien Amhara, Tigray, Oromia Englisch

የኦሮምያ መንግሥት ከመከላከያ ጎን ለመሰለፍ መዘጋጀቱን ማስታወቁ

የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በትግራዩ ጦርነት ለመሳተፍ የተገደደው ጉዳዩ የአገር ሉዓላዊነት መሆኑን በመረዳት ነው ሲል ክልሉ ትናንት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስትና ሕዝብ የሀገር ሉዓላዊነት ጋሻ ከሆነው የመከላከያ ሠራዊት ጎን በመሆን መስዋእትነት ለመክፈል ዝግጁ ነው ያለው መግለጫው ለክልሉ ማህበረሰብም የድጋፍ ጥሪ አቅርቧል።መግለጫው ህዋሓትን በህዝቦች መሀከል ቁርሾና ክፍፍል በመፍጠር እንዲሁም የአገር ፍቅር እንዲሸረሸር በማድረግ ኮንኗል።የክልሉን መንግስት መግለጫን በውል መረዳታቸውን የሚገልጹት የአምቦ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ መመህር አቶ ሰለሞን ተፈራ መልእክቱን በአዎንታዊም በአሉታዊም እንደተመለከቱት ይገልጻሉ። ዝርዝሩን ዘገባ ስዩም ጌቱ ከአዲስ አበባ ልኮልናል።
ስዩም ጌቱ 
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ