1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

 የእነጃዋር መሐመድ የፍርድ ቤት ሙግት

ረቡዕ፣ ግንቦት 18 2013

በጀዋር መሐመድ የክስ መዝገብ የተከሰሱት ፖለቲከኞች ለፍርድ ቤት በፅሁፍ ባቀረቡት አቤቱታ እንዳሉት ረጅም ቀጠሮ እንዲሰጣቸዉ የጠየቁት “በፍርድ ቤቱ ላይ እምነት ቢኖረንም አስፈጸሚዉ አካል በሂደቱ ጣልቃ እንደሚገባ በመመልከታችን ነው” ብለዋል

https://p.dw.com/p/3u00w
Äthiopien Oberlandesgericht Lideta
ምስል Seyoum Getu/DW

ቀጠሮዉ በ2 ዓመት እንዲራዘም ተከሳሾች ጠየቁ

 ሕዝብን ከሕዝብ ለማጋጨት በመሞከር፣ ሁከት በማነሳሳትና በሌሎች የሽብር ወንጀሎች የተከሰሱት የኦሮሞ ፖለቲከኞች የፍርድ ቤት ሙግታቸዉ ቀጠሮ በሁለት ዓመት እንዲራዘም ዛሬ በፅሁፍ ጠየቁ።በኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ መስራችና የኦሮሞ ፌደራሊስ ጎንግረስ (ኦፌኮ) አባል በጀዋር መሐመድ የክስ መዝገብ የተከሰሱት ፖለቲከኞች ለፍርድ ቤት በፅሁፍ ባቀረቡት አቤቱታ እንዳሉት ረጅም ቀጠሮ እንዲሰጣቸዉ የጠየቁት “በፍርድ ቤቱ ላይ እምነት ቢኖረንም አስፈጸሚዉ አካል በሂደቱ ጣልቃ እንደሚገባ በመመልከታችን ነው” ብለዋል፡፡አዲስ አበባ ያስቻለው የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት የአቃቤ ህግ የምስክሮች አሰማም ሂደት ላይ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰጠውን ብይን ግልባጭ በመመልከት አቃቤ ህግ  ማመልከቻውን እንዲያቀርብ አዟል፡፡

ስዩም ጌቱ 

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሰ