1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የእነእስክንድር የፍርድ ቤት ውሎ

ረቡዕ፣ ሐምሌ 14 2013

ዛሬ ሊደመጥ ቀጠሮ ተይዞለት የነበረው የእነ አቶ እስክንድር ነጋ የአቃቤ ሕግ ምስክርነት በፌደራል ሰበር ሰሚ ችሎት ታገደ። ከዛሬው የፍርድ ቤት ውሎ በኋላ ለሐምሌ 29 2013 ቀጠሮ ተሰጥቷል።

https://p.dw.com/p/3xnxA
Symbolbild Gericht Gesetz Waage und Hammer
ምስል Fotolia/Sebastian Duda

«ለሐምሌ 29 ተቀጥሯል»

ዛሬ ሊደመጥ ቀጠሮ ተይዞለት የነበረው የእነ አቶ እስክንድር ነጋ የአቃቤ ሕግ ምስክርነት በፌደራል ሰበር ሰሚ ችሎት ታገደ። አቃቤ ሕግ ምስክሮቼ በዝግ ችሎት እና ከመጋረጃ ጀርባ ይሰሙልኝ ብሎ ያመለከተውን ውድቅ ያደረገው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደኛ የጸረ ሽብርና ሕገ መንግሥታዊ ወንጀሎች ችሎት ከዛሬ ጀምሮ ለአምስት ተከታታይ ቀናት የአቃቤ ሕግ ምስክሮችን ለማድመጥ ተሰይሞ ነበር። ሆኖም ከዛሬው የፍርድ ቤት ውሎ በኋላ ለሐምሌ 29 2013 ቀጠሮ መሰጠቱን ከአዲስ አበባ ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር የላከው ዘገባ ያመለክታል።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ