1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የእነ አቶ ጃዋር ክስ የምስክሮች ቃል ሂደት እና የመዝገብ እግድ

ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 5 2013

ዛሬ በአዲስ አበባ ያስቻለው የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ከዛሬ ሚያዚያ 05 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ ሊሰማ የነበረው የአቃቤ ህግ ምስክሮች ቃል፤ ከሳሽ ይግባኝ በመጠየቁ መዝገቡ መታገዱን አሳውቋል፡፡፡

https://p.dw.com/p/3rx8o
Hammer Gerichtssaal Gericht Richter-Hammer
ምስል Adrian Wyld/empics/picture alliance

በእነ አቶ ጀዋር መሐመድ የተጠረጠሩ ተከሳሾች ፍርድ ቤት ቀርበዋል

ዛሬ በአዲስ አበባ ያስቻለው የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ከዛሬ ሚያዚያ 05 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ ሊሰማ የነበረው የአቃቤ ህግ ምስክሮች ቃል፤ ከሳሽ ይግባኝ በመጠየቁ መዝገቡ መታገዱን አሳውቋል፡፡፡
የአቃቤ ህግ የምስክሮች ቃል እንዲሰማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከዛሬ ጀምሮ ያሉትን ተከታታይ ሶስት ቀናት ሰጥቶ የነበረ ቢሆንም አቃቤ ህግ ምስክሮቼ ለደህንነታቸው ሲባል ከመጋረጃ ጀርባ እንዲደመጡ ያለው አቤቱታ ውድቅ መደረጉን ተከትሎ ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቤት ብሏል፡፡
ይህንኑን በዛሬ ችሎት ይፋ ያደረገው ከፍተኛ ፍርድ ቤት በነገው እለት ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሂደቱ ላይ ተከሳሾች በፕላዝማ ቀጥታ ከማረሚያ ቤት ገብተው የቃል ክርክር እንዲያደርጉ ትዕዛዝ መተላለፉን አሳውቋል፡፡
በሌላ በኩል አቶ በቀለ ገርባ በዛሬው ችሎት የኮቪድ-19 ክትባት እንዲሰጣቸው ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ እንዲያስተላልፍላቸው ጠይቀዋል፡፡
ስዩም ጌቱ 
ታምራት ዲንሳ
ማንተጋፍቶት ስለሺ