1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

 የእነ አቶ ጃዋር መሃመድ የህክምና ክርክር

ሐሙስ፣ የካቲት 18 2013

የወሕኒ ቤት ኃላፊዎችን የጠራዉ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት የታሰሩት አቶ በቀለ ገርባ ባለፈዉ የካቲት 11፣ ከፍርድ ቤቱ በተሰጣቸው ፍቃድ መሰረት ወደሚታከሙበት የግል ሐኪም ቤት ሲሔዱ ወደማይፈልጉት የመንግሥት ሆስፒታል ተገደዉ በመወሰዳቸዉ ሰበብ ነዉ

https://p.dw.com/p/3pvaS
Äthiopien Journalisten Martin Schibbye und Johan Persson
ምስል AP

የወሕኒ ቤቱ ኃላፊ ፍርድ ቤት ቀረቡ


የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የፀረ ሽብር እና ሐገ መንግስታዊ ጉዳዮች ችሎት የፍርድ ቤት ትዕዛዝ አላከበሩም ያላቸዉን  የወሕኒ ቤት ኃላፊዎችን ዛሬ ለጥያቄ ጠርቷል፡፡ፍርድ ቤቱ የወሕኒ ቤት ኃላፊዎችን የጠራዉ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት የታሰሩት አቶ በቀለ ገርባ ባለፈዉ የካቲት 11፣ ከፍርድ ቤቱ በተሰጣቸው ፍቃድ መሰረት ወደሚታከሙበት የግል ሐኪም ቤት ሲሔዱ ወደማይፈልጉት የመንግሥት ሆስፒታል ተገደዉ በመወሰዳቸዉ ሰበብ ነዉ።ከተከሳሽ ጠበቆች አንዱ እንዳሉት ዛሬ ችሎት የቀረቡት የማረሚያ ቤቶች ረዳት ኮሚሽነር ግርማ አደሬ ለችሎቱ ጥያቄ በሰጡት መልስ የፀጥታ ሥጋትን ምክንያት አቅርበዋል።ሕዝብን በማጋጨት ሙከራና በሌሎች ተያያዥ ወንጀሎች  ተጠርጥረዉ የታሰሩት የኦሮሞ ፖለቲከኞች የሕክምና ሥፍራና የሐኪሞቻቸዉ ማንነት እያወዛገበ ነዉ።

ስዩም ጌቱ 

ነጋሽ መሐመድ

ኂሩት መለሰ