1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ፖለቲካየመካከለኛው ምሥራቅ

የእስራኤል ፖለቲካ አንድምታ

ሰኞ፣ ግንቦት 30 2013

ላለፉት 12 ዓመታት ሥልጣን ላይ የቆዩትን የጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ አስተዳደር በተጣማሪ ፓርቲዎች ግፊት መንበሩን የመልቀቁ ሂደት አነጋጋሪ የፖለቲካ ድባብ በሀገሪቱ ላይ አስከትሏል።

https://p.dw.com/p/3uWkR
Proteste in Israel
ምስል Sebastian Scheiner/AP/dpa/picture alliance

በእስራኤል ወቅታዊው የፖለቲካ ይዞታ

ላለፉት 12 ዓመታት ሥልጣን ላይ የቆዩትን የጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ አስተዳደር በተጣማሪ ፓርቲዎች ግፊት መንበሩን የመልቀቁ ሂደት አነጋጋሪ የፖለቲካ ድባብ በሀገሪቱ ላይ አስከትሏል። በቀኝና በግራ የፖለቲካ ርዕዮተ ዓለም የተከፋፈሉት የእስራኤል ፖለቲከኖች የሀገሪቱን ከፍተኛ ሥልጣን ለመቆናጠጥ አንዳቸው በሌላቸው ላይ የሚሰነዝሩት ትችት ሀገሪቱን ወደ አለመረጋጋት ሊገፋ ይችላል የሚል አስተያየት እየተሰጠበት ነው። ኔታንያሁ እሳቸውን ከሥልጣን ለማስወገድ የተሰባሰቡ ተቀናቃኞቻቸውን በተመለከተ «አስጊ የሆነ የግራ ዘመም ርዕዮተ ዓለም ፖለቲከኞች ወደ ሥልጣን መምጣታቸው አደገኛ ነው የሚል አስተያየት መስጠታቸው» ተቀናቃኞቻቸውን አስቆጥቷል። የሀገሪቱ የደህንነት ዘርፍ የፖለቲከኞቹ መካከር አመጽ ሊቀላቀልበት ይችላል የሚል ስጋቱን በመግለጽ አስጠንቅቋል። የእስራኤል ፖለቲካ ግለትና ወዴት እያመራ ነው የሚለውን ለመቃኘት ወደኢየሩሳሌም በመደወል ዜናነህ መኮንን አነነጋግሬዋለሁ።

ዜናነህ መኮንን

ሸዋዬ ለገሠ

ማንተጋፍቶት ስለሺ