1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የእስረኞችን መተፋፈግ ለመቀነስ ማሸጋሸግ መጀመሩን የፌደራል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን አስታወቀ

ሰኞ፣ መጋቢት 14 2012

በማረሚያ ቤቶች ውስጥ ያለውን መተፋፈግ ለመቀነስ በጠባብ ክፍሎች ውስጥ የሚኖሩ ብዙ ታራሚዎችን የማሸጋሸግ ስራ መጀመሩን የፌደራል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን አስታወቀ። በማረሚያ ቤቶች የእስረኞች ጉብኝት ተከልክሏል። ይኸ የእስረኞችን ቤተሰቦች፤ የሐይማኖት መሪዎች እና ጠበቆቻቸውን ይጨምራል።

https://p.dw.com/p/3Zv8w
Äthiopien Kaliti Gefängnis
ምስል DW/Y. Gebregziabher

በማረሚያ ቤቶች የእስረኞች ጉብኝት ተከልክሏል

በማረሚያ ቤቶች ውስጥ ያለውን መተፋፈግ ለመቀነስ በጠባብ ክፍሎች ውስጥ የሚኖሩ ብዙ ታራሚዎችን የማሸጋሸግ ስራ መጀመሩን የፌደራል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን አስታወቀ።
የኮሮና ቫይረስ የስርጭትን ፍጥነትን ለመግታት የታራሚ ጠያቂዎች ለአስራ አምስት ቀናት እንዲታገዱ መደረጉ ለስራው መልካም አጋጣሚ መሆኑን የገለጸድ የቃሊቲ ከፍተኛ ጥበቃ ማረሚያ ቤት የተቋሙ ሰራተኞች ከንክኪ ጋር በተያያዘ በፍተሻ ስራ ላይ ቅሬታ አቅርበው እንደነበር አስታውቋል።
መንግስት ከእስር እንዲፈቱ የወሰነላቸውን ሰዎች በተመለከተ የሚፈቱት እነማን ናቸው የሚለው ሁለት ጊዜ ከተፈተሸ በኋላ ከሶስት ወይም አራት ቀናት በኋላ ታውቆ ከእስር ይወጣሉ ተብሏል።
በፌደራል ማረሚያ ቤቶች ከ 7670 በላይ እንዲሁም በቀጠሮ 2269 ታራሚዎች መኖራቸውን ከፌደራል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን የተገኘው መረጃ ይጠቁማል።
ሰለሞን ሙጬ
ኂሩት መለሰ