የኤርትራዉ ፕሬዚዳንት የኢትዮጵያ ጉብኝት በፖለቲካ ምሁሩ እይታ
ዓርብ፣ ጥቅምት 6 2013ማስታወቂያ
ለሦስት ቀናት የሥራ ጉብኝት ትናንት ሰኞ ማለዳ ድንገት ኢትዮጵያ የገቡት የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር የጅማ ዩኒቨርሲቲን የሥራ እንቅስቃሴዎች እንዲሁም በጅማ ዞን ጎማ ወረዳ አንድስኬታማ የቡና ማሳን ጎብኝተዋል። ፕሬዚደንት ኢሳያስ ዛሬ የኮይሻ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብን ብሎም የኢትዮጵያን ታላቁን የሕዳሴ ግድብ ከጠቅላይ ሚኒስርት ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ጋር በጋራ መጎብኘታቸዉን የተለያዩ የሃገር ዉስጥ መገናኛዎች የፎቶግራፍ ምስሎችን በማስደገፍ ዘግበዋል። የፕሬዚደንት ኢሳያስ አፈወርቂ የኢትዮጵያ ጉብኝት እንዴት ይገመገማል? የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ዮሃንስ ገብረግዚአብሔር አንድ የፖለቲካ ሳይንስ ምሁርን አነጋግሮ ዘገባ ልኮልናል ።
ዮሃንስ ገብረግዚአብሔር
አዜብ ታደሰ
ሸዋዬ ለገሠ