የኦነግ ክስና የመንግስት ምላሽ
ረቡዕ፣ ሰኔ 2 2013ማስታወቂያ
በአቶ ዳውድ ኢብሳ ሊቀመንበርነት የሚመራው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦ.ነ.ግ.) ሰሞኑን በተደጋጋሚ በይፋዊ የማኅበራዊ ሚዲያ ገጹ የኤርትራ ጦር ሰራዊት በኦሮሚያ በተለያዩ አከባቢዎች ይንቀሳቀሳሉ ብሏል። በሊቀመንበሩ አቶ ዳውድ ኢብሳ ጊዜያዊ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ሆነው መሰየማቸውን የሚገልጹት አቶ ለሚ ገመቹ ለዶይቼ ቬለ እንዳሉት ጦሩ ቀደም ሲል በምዕራብ ኦሮሚያ አሁን ደግሞ በደቡብ ኦሮሚያ እየተንቀሳቀሰ ነው። ስለ ጉዳዩ የተጠየቁት የኦሮሚያ ክልል ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ጌታቸው ባልቻ መረጃውን መሰረተ ቢስ ሲሉ አጣጥለውታል። ሥዩም ጌቱ ከአዲስ አበባ ተጨማሪ ዘገባ ልኮልናል፡፡
ሥዩም ጌቱ
ኂሩት መለሰ
ማንተጋፍቶት ስለሺ