1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢጋድ ስብሰባና የኢትዮጵያና የሱዳን የድንበር ኮሚሽን ጉባኤ

ሰኞ፣ ታኅሣሥ 12 2013

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከስብሰባው ጎን ለጎን ከኢጋድ አባል  መሪዎች ጋር መወያየታቸውን የገለፁት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ የሱዳን ሚሊሺያ ሰሞኑን ወደ ኢትዮጵያ ገብቶ በሰነዘረው "የሱዳን መንግሥት የማያውቀው"ባሉት ትንኮሳ እና መሰል ጉዳዮች ከሱዳን አቻቸው ጋር መምከራቸውንም ተናግረዋል።

https://p.dw.com/p/3n1Rl
IGAD Logo

የኢጋድ ስብሰባና የኢትዮጵያና የሱዳን የድንበር ኮሚሽን ጉባኤ

የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ኢጋድ አባል ሀገራትና የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን መሪዎች ትናንት በጅቡቲ በተካሄደው ውይይት ላይ የኢትዮጵያን የውስጥ ሕግ የማስከበር እርምጃ መደገፋቸው የዲፕሎማሲ ስኬት ውጤት ነው ሲል የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለፀ።ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከስብሰባው ጎን ለጎን ከኢጋድ አባል  መሪዎች ጋር መወያየታቸውን የገለፁት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ የሱዳን ሚሊሺያ ሰሞኑን ወደ ኢትዮጵያ ገብቶ በሰነዘረው "የሱዳን መንግሥት የማያውቀው"ባሉት ትንኮሳ እና መሰል ጉዳዮች ከሱዳን አቻቸው ጋር መምከራቸውንም ተናግረዋል።የሁለቱ ሀገራት የድንበር ኮሚሽን ጉባኤም ነገ ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል።ሰሎሞን ሙጬ ከአዲስ አበባ ዝርዝሩን አዘጋጅቷል።
ሰሎሞን ሙጬ
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ