ኢድ አል አድሃ በሳዑዲ
ማክሰኞ፣ ነሐሴ 15 2010ማስታወቂያ
ሳዑዲ አረቢያ ዉስጥ የኢድ አል-አድሃ በዓል ዛሬ በይፋ የተጀመረዉ መካ ዉስጥ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሑጃጆች ባደረጉት የስግደት ፀሎት ነዉ። በፀሎቱ ላይ የሳዑዲ አረቢያዉ ንጉስ እና የሐገሪቱ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ተገኝተዋል። እዚያዉ ሳዑዲ አረቢያ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያንም በዓሉን በመንፈሳዊ ሥርዓት አክበረዉ ዉለዋል። ለሐጅ ሥርዓት እዚያዉ ሳዑዲ አረቢያ የሚገኙት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ጉባኤ ፕሬዝደንት ሐጂ መሐመድ አሚን ጀማል ለመላዉ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል። የጂዳዉ ወኪላችን ነብዩ ሲራክ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።
ነብዩ ሲራክ
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ