የኢዴፓ እና ኢሃን አመራሮች ሕብር ኢትዮጵያ ፓርቲን ተቀላቀሉ
ዓርብ፣ ጥር 21 2013ማስታወቂያ
ሕጋዊ የፖለቲካ ፓርቲ ሰውነታቸው በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተሰረዙት የኢዴፓ እና የኢሃን ፓርቲዎች ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ ሙሉ አባላቶቻቸው ሕብር ኢትዮጵያ ፓርቲን በአባልነት ተቀላቀሉ።
ሕብር ኢትዮጵያ በኢትዮጵያ ፓለቲካ ውስጥ ጉልህ ድርሻ ያላቸው ያላቸውን እነዚህን አመራሮች በሙሉ አባልነት ሲቀበል ያላቸው ልምድ፣ እውቀትና ተሳትፎ ከፓርቲው በላይ ለሀገር ጠቃሚ መሆኑን እንደሚያምን ገልጿል።
የሁለቱ የቀድሞ ፓርቲዎች አመራሮች ሕብር ኢትዮጵያ ውስጥ ሆነው አብሮነት ያራምደው የነበረውን አቋም አሁንም እንደሚያስቀጥሉ ተናግረዋል።
ሰለሞን ሙጬ
አዜብ ታደሰ