1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የ«ኢየሩሳሌም የህፃናትና ማህበረሰብ ልማት»ፕሮጀክቶችና የዘጌ ገዳም ተጠቃሚዎቹ 

ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 21 2013

ድርጅቱ በአካባቢው በመሰረታቸው ትምሕርት ቤቶች ተማሪዎች ከመኖሪያቸው ሳይርቁ መማር መቻላቸውን እንዲሁም እናቶች በየቤታቸው ውሀ በአቅራቢያቸው ማግኘት መቻላቸውን መስክረዋል። ድርጅቱ እንደሚለው ከ35 ሚሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የተለያዩ ተቋማትን አስገንብቷል። የባሕር ዳር አስተዳደር ድርጅቱ ለሌሎች አርአያ የሚሆን ሥራ ማከናወኑን አረጋግጧል።

https://p.dw.com/p/3nNwv
Äthiopien Schulprojekt
ምስል Alemnew Mekonnen/DW

የ«ኢየሩሳሌም የህጻናትና ማኅበረሰብ ልማት ፕሮጀክቶች»ና ተጠቃሚዎቹ

«ኢየሩሳሌም የህፃናትና ማህበረሰብ ልማት» የተባለ አገር በቀል ድርጅት በዘጌ ገዳም ባደረጋቸው የልማት ስራዎች ተጠቃሚ መሆናቸውን በአካባቢው የሚኖሩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ተናገሩ።ድርጅቱ በአካባቢው በመሰረታቸው ትምሕርት ቤቶች ተማሪዎች ከመኖሪያቸው ሳይርቁ መማር መቻላቸውን እንዲሁም እናቶች በየቤታቸው ውሀ በአቅራቢያቸው ማግኘት መቻላቸውን መስክረዋል። ድርጅቱ እንደሚለው ከ35 ሚሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የተለያዩ ተቋማትን አስገንብቷል። የባሕር ዳር አስተዳደር ድርጅቱ ለሌሎች አርአያ የሚሆን ሥራ ማከናወኑን አመልክቷል። አብዛኞቹ ተቋማት የተገነቡት የጀርመን መንግስት ባደረገው የገንዘብ ድጋፍ እንደሆነም ተገልጧል።አለምነው መኮንን ከባህርዳር ተጨማሪ አለው።
ዓለምነው መኮንን
ኂሩት መለሰ
ማንተጋፍቶት ስለሺ