1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢዜማ ማሳሰቢያ

ሰኞ፣ ነሐሴ 10 2013

ኢዜማ ችግሮች በኃይል አማራጭ ብቻ በዘለቄታው ይፈታሉ የሚል እምነት እንደሌለው ገልፆ ሕወሓት አሁን ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ያለው እና አደጋ የደቀነው በአማራ እና አፋር ክልሎች ቢሆንም ይህን ጉዳትና አደጋ ባስቸኳይ ማቆም ካልተቻለ ሳይውል ሳያድር በሁሉም የአገሪቱ አካባቢዎች መከሰቱ እንደማይቀር አሳስቧል።

https://p.dw.com/p/3z3Q2
Äthiopien | Pressekonferenz EZEMA
ምስል Solomon Muchie/DW

«ብሔራዊ የሀገር ሉዓላዊነት እና የሕዝብ ደህንነት ማሰከበር ዘመቻ ግብረ ኃይል» በአስቸኳይ እንዲቋቋም

«ብሔራዊ የሀገር ሉዓላዊነት እና የሕዝብ ደህንነት ማሰከበር ዘመቻ ግብረ ኃይል» በአስቸኳይ እንዲቋቋም እና ወደ ሥራ እንዲገባ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትሕ ( ኢዜማ ) ጠየቀ። ፓርቲው ይህ ግብረኃይል በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ አገር አድን ሥራዎች እንዲፈፀሙ ውሳኔ የሚያስተላልፍ እንደሚሆንም ገልጿል። ኢዜማ ችግሮች በኃይል አማራጭ ብቻ በዘለቄታው ይፈታሉ የሚል እምነት እንደሌለው ገልፆ ሕወሓት አሁን ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ያለው እና አደጋ የደቀነው በአማራ እና አፋር ክልሎች ቢሆንም ይህን ጉዳትና አደጋ ባስቸኳይ ማቆም ካልተቻለ ሳይውል ሳያድር በሁሉም የአገሪቱ አካባቢዎች መከሰቱ የማይቀር መሆኑን አመልክቷል።

ሰሎሞን ሙጬ 

ሸዋዬ ለገሠ

አዜብ ታደሰ