የድጋፍ እና የተቃውሞ ሰልፍ በፓሪስ
ቅዳሜ፣ ሰኔ 29 2011ማስታወቂያ
ዛሬ ፓሪስ ፈረንሳይ ውስጥ ኢትዮጵያውያን የኢትዮጵያን መንግሥት የሚቃወሙ እና የሚደግፉ ሰልፎች በተመሳሳይ ቦታ በተመሳሳይ ሰዓት አካሂደዋል። የተቃውሞውን ሰልፍ ያስተባበረው በፈረንሳይ የአማራ ማህበር ነው።አስተባባሪዎቹ የሰልፉ ዓላማ በኢትዮጵያ ስርዓቱ በአማራ ላይ ያደርሳል የሚሉትን በደል ለማሳወቅ መሆኑን ለዶቼቬለ ተናግረዋል።ሌላኛ ሰልፍ ደግሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የሚመሩትን ከዛሬ አንድ ዓመት ወዲህ የሚካሄደውን ለውጥ እና የመንግሥታቸውን እርምጃ በመደገፍ የተካሄደ ነበር። የዚሁ ሰልፍ ተካፋዮች ፣የዶክተር አቢይን ስም ለማጥፋት መጡ ላሏቸው ተቃዋሚዎች ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥፋተኛ እንዳልሆኑ እና ለሁሉም ዜጎች እንደሚሰሩ ለማመልከት መሰለፋቸውን ተናግረዋል።በስፍራው የተገኘችው የፓሪስዋ ዘጋቢያችን ሃይማኖት ጥረነህ ቀጣዩን ዘገባ አጠናቅራለች።
ኃይማኖት ጥሩነህ
ኂሩት መለሰ