1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢትዮጵያውያን በፓሪስ ያካሄዱት ውይይት 

ዓርብ፣ መጋቢት 27 2011

በፈረንሳይ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጋር በተካሄደ ውይይት ጥሪውን ያስተላለፈው ኤምባሲው ዜጎችን ለማገልገል ዝግጁ መሆኑንን አስታውቋል። በፈረንሳይ አዲሱ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሔኖክ ተፈራ ከኢትዮጵያውያን ጋር በተዋወቁበት በዚሁ መድረክ ላይ በኤምባሲው ኢትዮጵያውያን ለመሰባሰቢያ እና ለተለያዩ ዝግጅቶች ማካሄጃ የሚጠቀሙበት ቦታ መዘጋጀቱን ተናግረዋል።

https://p.dw.com/p/3GN4y
Frankreich | neuer Botschafter Äthiopiens Henok Tefera in Paris
ምስል DW/H. Turuneh

ኢትዮጵያውያን በፓሪስ ያካሄዱት ውይይት 

ፈረንሳይ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በተለያዩ ዘርፎች ሀገራቸውን ሊያግዙ እንደሚገባ ተጠየቀ። ባለፈው ሳምንት መጨረሻ  ፓሪስ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በተዘጋጀ ልዩ መድረክ ላይ በፈረንሳይ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጋር በተካሄደ ውይይት ጥሪውን ያስተላለፈው ኤምባሲው፣በበኩሉ ዜጎችን ለመርዳት እና ለማገልገል ዝግጁ መሆኑንን አስታውቋል። በፈረንሳይ አዲሱ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሔኖክ ተፈራ በዚያ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጋር በተዋወቁበት በዚሁ መድረክ ላይ በኤምባሲው ኢትዮጵያውያን ለመሰባሰቢያ እና ለተለያዩ ዝግጅቶች ማካሄጃ የሚጠቀሙበት ቦታ መዘጋጀቱን ተናግረዋል። የፓሪስዋ ወኪላችን ሃይማኖት ጥሩነህ ዝርዝሩን ልካልናለች።
ሃይማኖት ጥሩነህ 
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ