1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያው ጦርነትና የድርድር ጥያቄ

እሑድ፣ ታኅሣሥ 17 2014

ተዋጊዎቼ ከአማራና ከአፋር ክልሎች እንዲያፈገፍጉ አዝዣለሁ ያለው ህወሓት  የተኩስ አቁምና የድርድር ጥያቄ የያዘ ደብዳቤ ለተመድ ዋና ጸሐፊ አንቶንዮ ጉተሬሽ ልኳል። መንግሥት በበኩሉ ህወሓት ተዋጊዎቼ እንዲወጡ አዝዣለሁ ማለቱን «በኢትዮጵያ ኃይሎች የደረሰበትን ሽንፈት ለመሸፋፈን የፈጠረው ማደናገሪያ» ሲል አጣጥሎታል።

https://p.dw.com/p/44oeE
Äthiopien Tigray-Konflikt | Armee übernimmt wieder Kontrolle
ምስል Minasse Wondimu Hailu/AA/picture alliance

የኢትዮጵያው ጦርነትና የድርድር ጥያቄ

ከአንድ ዓመት በላይ ባስቆጠረውና አሁንም በቀጠለው የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊትና የአማራ ክልል ኃይሎች ፣ ከሳምንታት ወዲህ በህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ህወሓት ተይዘው የነበሩ የተለያዩ ከተሞችን መልሰው እየተቆጣጠሩ ነው።ከዚሁ ጋር መንግሥት በተለያዩ አካባቢዎች ተበታትነው የሚገኙ የህወሓት ኃይሎችን «እያጸዳሁ» ነው ሲል አስታውቋል ።በዚህ መሀል ተዋጊዎቼ ከአማራና ከአፋር ክልሎች እንዲያፈገፍጉ አዝዣለሁ ያለው ህወሓት  የተኩስ አቁምና የድርድር ጥያቄ የያዘ ደብዳቤ ለተመድ ዋና ጸሐፊ አንቶንዮ ጉተሬሽ ልኳል። መንግሥት በበኩሉ ህወሓት ተዋጊዎቼ እንዲወጡ አዝዣለሁ ማለቱን «በኢትዮጵያ ኃይሎች የደረሰበትን ሽንፈት ለመሸፋፈን የፈጠረው ማደናገሪያ» ሲል አጣጥሎታል። የመንግሥት ባለሥልጣናት «አሸባሪ» ከሚሉት ከህወሓት ጋር ድርድር እንደማይኖር  ተናግረዋል።

በዚህ ወቅት ላይ ታዲያ የህወሓት የድርድር ጥያቄ ምን ትርጉም አለው? ጦርነቱ እንዲያበቃና በሀገሪቱ ሰላም እንዲሰፍን ምን ዓይነት ተጨባጭ እርምጃዎች ሊወሰዱ ይገባል? የዛሬው እንወያይ ትኩረት ነው ።በዚህ ርዕስ ላይ የሚወያዩ ሁለት እንግዶች አሉን። እነርሱም ዶክተር አደም ካሴ ዘ ሔግ ኔዘርላንድስ የሚገኘው ዓለም አቀፍ የዴሞክራሲና የምርጫ ድጋፍ ሰጪ ተቋም፣ የሕገ-መንግሥትና የዴሞክራሲ ግንባታ አጥኚና አማካሪ፣  አቶ ሙሉጌታ አበበ የመኢአድ ምክትል ሊቀ መንበርና የአዲስ አበባ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ ናቸው።ሙሉውን ውይይት ለመከታተል ከታች የሚገኘውን የድምጽ ማዕቀፍ ይጫኑ

ኂሩት መለሰ