1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያው ቀውስና የድርድር ፈተና

ረቡዕ፣ መስከረም 12 2014

ኢትዮጵያ አሁን ለገባችበት የፖለቲካ እና ሰላም እጦት ቀውስ መፍትሄው ድርድር እና ብሔራዊ ምክክር ብቻ መሆኑን የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ ባለስልጣን አመለከቱ፡፡ የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግሬስ (ኦፌኮ) ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጥሩነህ ገምታ እንዳሉት ችግሮችን በማቃለል ሊደርስ የሚችለውን የባሰ ቀውስ ለማስቀረት ለሰላም መንገድ ዋጋ መከፈል ይኖርበታል ፡፡

https://p.dw.com/p/40fL1
Karte Äthiopien englisch

የኢትዮጵያ ወቅታዊ ቀውስ እና የድርድር መፍትሄው ፈተና


ኢትዮጵያ አሁን ለገባችበት የፖለቲካ እና ሰላም እጦት ቀውስ መፍትሄው ድርድር እና ብሔራዊ ምክክር ብቻ መሆኑን የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ ባለስልጣን አመለከቱ፡፡
የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግሬስ (ኦፌኮ) ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጥሩነህ ገምታ በተለይ ለዶይቼ ቬለ እንዳሉት ችግሮችን በማቃለል ሊደርስ የሚችለውን የባሰ ቀውስ ለማስቀረት ለሰላም መንገድ ዋጋ መከፈል ይኖርበታል ፡፡
በአንጻሩ የኢትዮጵያ መንግስት አሁን የገባበት የጦርነት ቀውስ አስገዳጅ መሆኑን የሚያነሱት በአምቦ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ ባለሙያ በምዕራባውያን የሚደረግ የሰላም ግፊትም ቢሆን መጤን ያለበት ነው ብለዋል፡፡ 
ስዩም ጌቱ 
ታምራት ዲንሳ
ማንተጋፍቶት ስለሺ