1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢዴፓ)  ምርጫው እንዲራዘም ጠየቀ 

ረቡዕ፣ ነሐሴ 15 2011

ምርጫው እንዲራዘም የጠየቀው አገሪቱ ውስጥ አስተማማኝ ሰላምና መረጋጋት ባለመኖሩ ፣ መንግስት በሁሉም የሃገሪቱ ክፍል ህግና ስርዓትን በብቃት ማስከበር ባለመቻሉ እና ምርጫ ቦርድ ነጻና ፍትሃዊ ምርጫ ማከናወን የሚችልበት ዝግጅት ላይ ባለመሆኑ እንደሆነ አስታውቋል።

https://p.dw.com/p/3OHkJ
Äthiopien PK Ethiopian democratic party
ምስል DW/S. Mushie

የኢዴፓ መግለጫ

የኢትዮጵያዊያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ በምህጻሩ አዴፓ ለመጪው ዓመት የታቀደው ምርጫ እንዲራዘም ጠየቀ። ፓርቲው ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ በሰጠው መግለጫ  ምርጫው እንዲራዘም የጠየቀው አገሪቱ ውስጥ አስተማማኝ ሰላምና መረጋጋት ባለመኖሩ ፣ መንግሥት በሁሉም የሃገሪቱ ክፍል ሕግና ሥርዓትን በብቃት ማስከበር ባለመቻሉ እና ምርጫ ቦርድ ነጻና ፍትሃዊ ምርጫ ማከናወን የሚችልበት ዝግጅት ላይ ባለመሆኑ እንደሆነ አስታውቋል። ፓርቲው በኢትዮጵያ ብሔራዊ  ምርጫ ቦርድ  ተፈጽሞብኛል ባለው ሕገ ወጥ  ጣልቃ ገብነት ከፍተኛ የህልውና ፈተና ላይ እንደነበር ጠቅሶ በዚህ ምክንያትም ምንም አይነት ድርጅታዊ ሥራ ሳያከናውን መቆየቱን አመልክቷል። የሀገሪቱን ወቅታዊ ሁኔታ በጥልቀት ምርምሬያለሁ ኢዴፓ በሀገሪቱ ከፍተኛ የለውጥ ስሜት እና ተነሳሽነት ተፈጥሮ የነበረ ቢሆንም በሂደት የለውጥ አመራሩ ሠራቸው ባላቸው ስህተቶች እና ሳይሰራቸው ቀሩ ባላቸው መሰረታዊ ጉዳዮች ምክንያት የለውጥ ሂደቱ በከፍተኛ ፍጥነት የመክሸፍ አደጋ ውስጥ እየገባ መሆኑን እንደተገነዘበ አመልክቷል።  መግለጫዉን የተከታተለዉ የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ሰለሞን ሙጬ ተጨማሪ ዘገባ አለዉ። 

ሰሎሞን ሙጬ

ኂሩት መለሰ

አዜብ ታደሰ