1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያዉያን የተቃዉሞ ሰልፍ

ሐሙስ፣ የካቲት 19 2012

የሕዳሴን ግድብ ግንባታና የዉኃ ቀሞላልን በተመለከተ ሱዳን ግብፅና ኢትዮጵያ በሚያካሂዱት ድርድር ዩናይትድ ስቴትስ ኢትዮጵያ ላይ እያሳረፈች ያለዉን ጫና ታንሳ ሲሉ በዋሽንግተን እና አካባቢዋ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ለተቃዉሞ አደባባይ ወጡ። ሰልፈኞቹ ያዘጋጁትን ደብዳቤ ለአሜሪካ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ለአሜሪካ የገንዘብ ሚኒስቴርም ይሰጣሉ።

https://p.dw.com/p/3YY0q
Äthiopiens DC Demonstration gegen US intervention
ምስል Privat

የአባይ ጉዳይ የሁላችንም ነዉ

የሕዳሴን ግድብ ግንባታና የዉኃ ቀሞላልን በተመለከተ ሱዳን ግብፅና ኢትዮጵያ በሚያካሂዱት ድርድር ዩናይትድ ስቴትስ ኢትዮጵያ ላይ እያሳረፈች ያለዉን ጫና ታንሳ ሲሉ በዋሽንግተን እና አካባቢዋ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን እና ትዉልደ ኢትዮጵያዉያን በአሁኑ ሰአት በዩናይትድ ስቴትስ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፊት ለፊት የተቃዉሞ ሰልፍ ወጥተዋል። ከሰልፉ አስተባባሪዎች አንዱ የሆኑት አቶ ጥበቡ አሰፋ ለዶቼ ቬለ እንደተናገሩት የአባይ ጉዳይ የኢትዮጵያዉያን ሁሉ ህልዉና ነዉ። በዩናይትድ ስቴትስ የምንገኝ ኢትዮጵያዉያን የአባይ ጉዳይ ያገባናል፤ ጉዳዩን ችላ ብለን አንተዉም ያሉት ሰልፈኞቹ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድም ጥሪያቸዉን አስተላልፈዋል። ሰልፈኞቹ አሜሪካ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ለአሜሪካ የገንዘብ ሚኒስቴር ይህንኑ ጥያቄያቸዉን በደብዳቤ መልክ አዘጋጅተዉ በእጅ እንደሚሰጡ የሰልፉ አስተባባሪ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል።

አዜብ ታደሰ

ማንተጋፍቶት ስለሺ