1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያዉያን ስጋት፣የፖለቲካ ተንታኙ አስተያየት

ማክሰኞ፣ መጋቢት 19 2015

የፖለቲካ ስልጣን በበላይነት ለመያዝ፣ በጦርነቱና በግዛት ይገባኛል ሰበብ የሚሻኮቱት የአማራና የትግራይ ብሔረተኞች በስምምነቱ ማግስት በየፊናቸዉ ታክቲካዊ የፖለቲካ አጋር ፍለጋ እየጣሩ መሆናቸዉም በሰፊዉ እየተነገረ ነዉ።

https://p.dw.com/p/4POXn
Äthiopien Yared Tibebu
ምስል Government Communication Affairs Office/Kewot Woreda

የኢትዮጵያዉያን ሥጋት፣ የአቶ ያሬድ አስተያየት

የኢትዮጵያ የፌደራል መንግስትና ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) ሰላም ማዉረዳቸዉ ከዉጪም ከዉስጥም ብዙዎችን አስደስቷል።ይሁንና የኤርትራ ጦር ሙሉ በሙሉ የኢትዮጵያ ግዛትን ለቅቆ አለመዉጣቱ፣የትግራይና የአማራ ፖለቲከኞችን የሚያወዛግቡ ግዛቶች እጣ ፈንታ ግልፅ አልባት አለማግኘቱ የሌላ ጠብና ግጭት ሰበብ እንዳይሆን ማሳሰቡ አልቀረም።
የፖለቲካ ስልጣን የበላይነት ለመያዝ፣ በጦርነቱና በግዛት ይገባኛል ሰበብ የሚሻኮቱት የአማራና የትግራይ ብሔረተኞች በስምምነቱ ማግስት በየፊናቸዉ ታክቲካዊ የፖለቲካ አጋር ፍለጋ እየጣሩ መሆናቸዉም በሰፊዉ እየተነገረ ነዉ።
አንዳዶች እንደሚሉት የአማራ አክራሪ ብሔረተኞች የኤርትራን፣ የሕወሓት ደግሞ የኦሮሞን አክራሪ ብሔረተኞችን አጋርነት ለማግኘት እያሴሩ ነዉ።ደም የተቃቡት፣ለዓመታት ለመጠፋፋት የሚያደቡት የኤርትራና የሕወሃት ፖለቲከኞች ላጭር ጊዜም ቢሆን ከየሚጥሟቸዉ ወገኖች ጋር አበሩም አላበሩ በአማራና በኦሮሞ ልሒቃን መካከል የሚካሔደዉ ሽኩቻ «የአማራና የኦሮሞ ብልፅግና» በሚባሉት በገዢዉ ፓርቲ ቡድናት መካከል እንኳ በግልፅ እየታየ ነዉ።
ዛሬ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በተደረገ ዉይይት የተለያዩ አካባቢ እንደራሴዎች እንዳሉት ሽኩቻ፣መወቃቀስ፤መወጋገዙ በናረ ቁጥር ወትሮም በቅጡ ያልጠናዉ ወይም ሆን ተብሎ ቸል የተባለዉ በሐገሪቱ ሕግና ሥርዓት የማስከበር ርምጃ ጨርሶ እየተዘነጋ፣የዜጎች ደሕንነት ላደጋ እየተጋለጠ፣ ሰዎች በጠራራ ፀኃይ እየታገቱ፣እየተደበደ፣ እየተዘረፉ ነዉ።ኢትዮጵያ ባጠቃላይ የወደቀች፣የከሸፈች ወይም failed state ሆናለች የሚሉ ብዙዎች ናቸዉ።ዕዉቁ ኢትዮጵያዊ ተቃዋሚ ፖለቲከኛ ልደቱ አያሌዉ ጨርሶ የመንግስት መፍረስ እንዳይደርስ ያሰጋል ይላሉ።
የቀድሞዉ የኢሕዴን መስራችና የፖለቲካ ተንታኝ ያሬድ ጥበቡ ግን «አይ-አዎ» ባይ ናቸዉ።ሁለቱን ፖለቲከኛና የፖለቲካ ተንታኝ አነጋግረናል።ከአቶ ያሬድ ጋር የተደረገዉን ሙሉ ቃለ መጠይቅ እነሆ

የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት
የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትምስል Solomon Muchie/DW

ነጋሽ መሐመድ

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር