በአዉሮጳ የተለያዩ ሃገራት የሚገኙ ኢትዮጵያዉያን ብራስልስ ላይ ሰልፍ አካሄዱ፤
ሐሙስ፣ ጥቅምት 3 2009ማስታወቂያ
ከቤልጅግ፣ ከኔዘርላንድስ፣ ከፈረንሳይ እና ከጀርመን ወደብራስልስ እንደሄዱ የተገለጸዉ ኢትዮጵያዉያን፤ በሀገሪቱ የሚፈጸሙ ግድያዎች እና እስራትን የአዉሮጳ ኅብረት መሪዎች ለማስቆም ጥረት አድርጉ የሚል አቤቱታቸዉን በጽሑፍ አቅርበዋል። ከዚህም በተጨማሪ በቅርቡ ቢሾፍቱ ላይ በኢሬቻ በዓል ወቅት ለሞቱ እና ከዚያም በፊት በተለያዩ አጋጣሚዎች ህይወታቸዉን ላጡ ኢትዮጵያዉያን የመታሰቢያ የሻማ ማብራት ሥርዓትም እንዳደረጉ በስፍራዉ የተገኘዉ ዘጋቢያችን ገበያዉ ንጉሤ ገልጾልናል። ሰልፉ እየተካሄደ ባለበት ሰዓት ገበያዉን በስልክ አግኝቼዋለሁ፤
ገበያዉ ንጉሤ
ሸዋዬ ለገሠ
ነጋሽ መሐመድ