የኢትዮጵያን ቅርስ ለመመለስ የተዘጋጁት ትውልደ ኢትዮጵያዊ
ረቡዕ፣ መስከረም 21 2012ማስታወቂያ
ቅርሱ ወደ እሳቸው እጅ እንዴት እንደገባ ለጊዜው ለመናገር አልፈልግም ያሉት አቶ ሲራክ በ1626ዓ,ም በአጼ ፋሲለደስ ዘመነ መንግሥት የተሠራ ዘውድ በቤታቸው ከስጋት ጋር ይዘው መቆየታቸውን ለዶቼ ቬለ ገልጸዋል።
አቶ ሲራክ አስፋው የተባሉ እኚሁ ኢትዮ ሆላንዳዊ ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ እና አሥራ ሁለቱ ሐዋርያት የተቀረጹበትን ይህንን ዘውድ ፣ ቤታቸው በእንግድነት የመጣ ሰው ትቶት ከሄደው ሻንጣ ውስጥ እንዳገኙት ለአዣንስ ፍራንስ ፕረስ ተናግረዋል። ዘውዱን እንዳዩትም የተሰረቀ መሆኑን በማሰብ፣ ኢትዮጵያ እስካልተመለሰ ድረስ ከቤታቸው እንደማይወጣ ፣ ማንነታቸውን ይፋ ላላደረጉት ዘውዱ ለተገኘበት ሻንጣ ባለቤት መናገራቸውንም ገልጸዋል። በአሁኑ ጊዜ ዘውዱ ደህንነቱ በተጠበቀ ስፍራ እንደሚገኝ የተናገሩት አቶ ሲራክ፣ ይህን የኢትዮጵያ ታላቅ ቅርስ በቅርቡ ለኢትዮጵያ ባለሥልጣናት እንደሚያስረክቡም ተናግረዋል። ይህ ጥንታዊ ዘውድ ከወርቅ እና መዳብ መሠራቱ ነው የተነገረው። ስለቅርሱ ዛሬ ዜናውን ያፋ ካደረጉ በኋላ ወደሚገኙበት ስልክ በመደወል አነጋግረናቸዋል።
ሸዋዬ ለገሠ
አዜብ ታደሰ