የኢትዮጵያና የግብፅ ልዩነት
ሐሙስ፣ መስከረም 8 2012ማስታወቂያ
ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ በምታስገነባዉ ግዙፍ የኤሌክትሪክ ማመንጫ ግድብ ሰበብ ከግብፅ ጋር የገጠመችዉ አለመግባባት እስካሁን ሁነኛ መፍትሔ አላገኘም።የኢትዮጵያ፣የሱዳንና የግብፅ የዉኃ ሚንስትሮች ባለፈዉ ዕሁድና ሰኞ ካይሮ ዉስጥ ባደረጉት ስብሰባም መፍትሔ ላይ ሳይደርሱ በቀጠሮ ተለያይተዋል።የፖለቲካ ተንታኞች እንደሚሉት ሶስቱ ሐገራት በየፊናቸዉ የገጠማቸዉ ፖለቲካዊ ቀዉስ እስካሁን ለዘለቀዉ አለመግባባት ሌላ መልክና ባሕሪ እየሰጠዉ ነዉ።በመቀሌ ዩኒቨርስቲ የዉጪ ግንኙነት መምሕር አቶ የማነ ዘርዓት እንደሚሉት ደግሞ ግብፅ የኢትዮጵያና የሱዳን ወቅታዊን በመጠቀም ፍላጎቷን ለማስፈፀም እየጣረች ይመስላል።
ሚሊዮን ኃይለ ስላሴ
ነጋሽ መሐመድ
ኂሩት መለሰ