1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያና የአዉሮጳ ሕብረት ባለሥልጣናት ዉይይት

ረቡዕ፣ ኅዳር 16 2013

መንግስታቸዉ ስለሚወስደዉ ርምጃ ለተለያዩ መንግስታት ለማስረዳት የዲፕሎማሲ ዘመቻ የጀመሩት የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትርና የዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን በበኩላቸዉ ትናንት ብራስልስ ዉስጥ ለአዉሮጳ ሕብረት የዉጪ ጉዳይ ኃላፊ ለጆሴፍ ቦርየል ማብራሪያና ገለፃ አድርገዋል

https://p.dw.com/p/3lpTB
Stellvertretender Premierminister von Äthiopien - Demeke Mekonnen Hassen
ምስል G. Tiruneh

የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትርና የዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ጉብኝት በብራስልስ

የኢትዮጵያ ፌደራዊ መንግስትና የሕዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ የገጠሙት ጦርነት የዓለም አቀፍ ርዕስ ሆኗል።ጦርነቱ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታዉ ጥበቃ ምክር ቤት አባላትን ትናንት ማታ ሲያወዛግብ ነበር።የቀድሞዉ የሞዛምቢክ፣ የላይቤሪያና የደቡብ አፍሪቃ ፕሬዝደንቶችን የያዘዉ የአፍሪቃ ሕብረት የመልዕክተኞች ጓድ ዛሬ ወደ አዲስ አበባ መጓዙን ሰምተናል።መንግስታቸዉ ስለሚወስደዉ ርምጃ ለተለያዩ መንግስታት ለማስረዳት የዲፕሎማሲ ዘመቻ የጀመሩት የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትርና የዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን በበኩላቸዉ ትናንት ብራስልስ ዉስጥ ለአዉሮጳ ሕብረት የዉጪ ጉዳይ ኃላፊ ለጆሴፍ ቦርየል ማብራሪያና ገለፃ አድርገዋል።ቦርየል ኢትዮጵያ ዉስጥ እየተደጋጋመ የመጣዉ የብሔር ግጭት እንዳሰጋቸዉ አልሸሸጉም።

ገበያዉ ንጉሴ

ነጋሽ መሐመድ

ማንተጋፍቶት ስለሺ