የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ችግርና ዓለም አቀፉ ኅብረተሰብ
እሑድ፣ ነሐሴ 15 2008ማስታወቂያ
ለሰብዓዊ መብት የሚቆረቆሩ ተቋማት በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ የፀጥታ ኃይሉ በወሰደዉ ያልተመጣጠነ የኃይል ርምጃ የጠፋዉ የሰዉ ሕይወ እና የተጎዱት ሰዎች መጠን እና ሁኔታ እንዲጣራ በተደጋጋሚ ይጠይቃሉ። ዓለም አቀፉ ኅብረተሰብንም የሰብዓዊ መብቶችን ጥሰት በቸልታ በመመልከት ይተቻሉ። የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር በቅርቡ ኢትዮጵያ ዉስጥ ሰሞኑን የፀጥታ ኃይሉ የወሰደዉ የኃይል ርምጃ ያስከተለዉ ጉዳት በገለልተኛ ወገን እንዲጣራ ጠይቋል። አዎንታዊ ምላሽ ባያገኝም። የቀጠለዉ ተቃዉሞ፤ የመንግሥት የኃይል ርምጃ እና የዓለም አቀፉ ኅብረተሰብ የለዘበ አተያይ፤ የዚህ ሳምንት የዶቼ ቬለ የዉይይት ርዕሰ ጉዳይ ነዉ። ሙሉዉን ዉይይት ከድምጽ ዘገባዉ ያድምጡ።
ሸዋዬ ለገሠ
ልደት አበበ