የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች ድርድር
ዓርብ፣ የካቲት 17 2009ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ገዢ ፓርቲ፤ የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲ ግንባር (ኢሕአዴግ) እና የተለያዩ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ተወካዮች የጀመሩትን ድርድር ዛሬ ለሰወስተኛ ዙር ቀጥለዋል።ተወካዮቹ ድርድሩ ሥለሚደረግበት መርሕ በተረቀቀዉ ሐሳብ ላይ ከየፓርቲዎቻቸዉ ባለሥልጣናት ጋር ለመነጋገር ረቂቅ ሰነዱን ተከፋፍለዋል።በዛሬዉ ስብሰባ ድርድሩ ለመገናኛ ዘዴዎች ክፍት እንዲሆን የቀረበዉ ሐሳብ በተደራዳሪዎች ዘንድ ተቀባይነት ማግኘቱን የስብሰባዉ ተካፋዮች አስታዉቀዋል።የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ነጋሽ መሐመድ
ሸዋዬ ለገሰ