1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት መግለጫ

ዓርብ፣ የካቲት 13 2012

የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ቀጣዩ ሀገር አቀፍ ምርጫ መካሄድ የለበትም በሚል አቋሙ መጽናቱን ዐሳወቀ። የምክር ቤቱ ኃላፊዎች ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ምርጫው ይካሄድ ወይንም አይካሄድ በሚል ሰፊ ውይይት ከአደረጉ በኋላ በአብላጫ ድምፅ ምርጫው መኪያሄድ እንደማይገባው የጋራ ምክር ቤቱ መወሰኑን ይፋ አድርገዋል።

https://p.dw.com/p/3Y9N5
Äthiopien Musa Adem und Girna Bejele
ምስል DW/Y. G. Egziabher

ምርጫው መኪያሄድ የለበትም ሲል የጋራ ምክር ቤቱ ወስኗል

የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ቀጣዩ ሀገር አቀፍ ምርጫ መካሄድ የለበትም በሚል አቋሙ መጽናቱን ዐሳወቀ። የምክር ቤቱ ኃላፊዎች ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ምርጫው ይካሄድ ወይንም አይካሄድ በሚል ሰፊ ውይይት ከአደረጉ በኋላ በአብላጫ ድምፅ ምርጫው መኪያሄድ እንደማይገባው የጋራ ምክር ቤቱ መወሰኑን ይፋ አድርገዋል። ውሳኔው ላይ የተደረሰውም በየካቲት 7 ቀን፣ 2012 ዓ.ም የጋራ ምክር ቤቱ ባከናወነው ውይይት መኾኑን ጠቅሷል። የጋራ ምክር ቤቱ ምርጫው መደረግ አይገባውም የሚለው ውሳኔ ላይ የደረሰው በስድስት ተቃውሞ፤ አምስት ድምፀ-ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ መኾኑንም በጋዜጣዊ መግለጫው ወቅት ገልጧል።  የአዲስ አበባው ወኪላችን ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር ጋዜጣዊ መግለጫውን ተከታትሎ ቀጣዩን ዘገባ ልኮልናል። 


ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ኂሩት መለሰ