1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ጓድ ለኢትዮጵያ አንድነት 

ማክሰኞ፣ ነሐሴ 4 2013

በኢትዮጵያ ዲያስፖራ ማኅበረሰብ የሚስተዋለውን መከፋፈል ወደ ጎን በመተው በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ መተባበር ለመፍጠር እንቅስቃሴ መጀመሩን የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ጓድ የተባለ ስብስብ ገለፀ።

https://p.dw.com/p/3yo9M
Äthiopien | Professor Biruk Hailu
ምስል Solomon Muchie/DW

በአሜሪካ የሚገኙ 13 የሲቪክ ማኅበረሰብ ድርጅቶችን ያቀፈ ነዉ

በኢትዮጵያ ዲያስፖራ ማኅበረሰብ የሚስተዋለውን መከፋፈል ወደ ጎን በመተው በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ መተባበር ለመፍጠር እንቅስቃሴ መጀመሩን የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ጓድ የተባለ ስብስብ ገለፀ። ስብስቡ በአሜሪካ የሚገኙ 13 የሲቪክ ማኅበረሰብ ድርጅቶችን ያቀፈ እና ከስምንት ወራት በፊት የተመሰረተ ነው ተብሏል። ከሰሞኑ ወደ ኢትዮጵያ የገባው ይሄው የኢትዮጵያ ዲያስፖራ የሰላም ጓድ በግጭት ምክንያት ተፈናቅለው በመጠለያ ጣቢያዎች የሚገኙ ኢትዮጵያዊያንን ወደተለያዩ ክልሎች በመጓዝ ጎብኝቷል። አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ ያዘችው ያለውን የተሳሳተ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ለማሻሻል ብርቱ ግፊት እያደረገ መሆኑን በመጥቀስ ለዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ጆ ባይደን አስተዳደር ቅርበት አላቸው ያላቸውና ከትዮጵያ ጀርባ የቆሙ ኢትዮጵያዊያንን ግፊት ለመመከትም ተጨባጭ ሥራ እየከወነ መሆኑንም ስብስቡ ዛሬ አዲስ አበባ ላይ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።

ሰለሞን ሙጬ 
አዜብ ታደሰ 
ማንተጋፍቶት ስለሺ