1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አዲስ ተሽዋሚዋ ሚኒስትር ወ/ሮ ፍፁም አሰፋ

ሐሙስ፣ ጥቅምት 8 2011

በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ አዲስ ካቢኔ ውስጥ የኢትዮጵያ የፕላን እና የልማት ኮሚሽን ሚኒስቴር ሆነዉ ትናንት የተሾሙት ወ/ሮ ፍፁም አሰፋ ሹመቱን ጠብቀዉት እንዳልነበረ ሆኖም በጣም እንደተደሰቱ እና ለሳቸዉ ታሪካዊ አጋጣሚና መሆኑን ዛሬ «DW» ገለፁ። ሚኒስትርዋ በጀርመን የዶክትሬት ማዕረጋቸዉን ሊይዙ 4 ሳምንትነዉ የቀራቸዉ።

https://p.dw.com/p/36ixC
Fitsum Assefa
ምስል privat

አዲስ ተሽዋሚዋ ሚኒስትር ወ/ሮ ፍፁም አሰፋ

በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ አዲስ ካቢኔ ውስጥ የኢትዮጵያ የፕላን እና የልማት ኮሚሽን ሚኒስቴር ሆነዉ ትናንት የተሾሙት ወ/ሮ ፍፁም አሰፋ ሹመቱን ጠብቀዉት እንዳልነበረ ሆኖም ለሳቸዉ ታሪካዊ አጋጣሚና በጣም እንደተደሰቱ ለ «DW» ገለፁ። በጀርመን በግብርና ዘርፍ የዶክትሬት ማዕረግን ለመቀበል የሚያበቃቸውን ጥናት ለማጠናቀቅ ወደ አራት ሳምንት ገደማ እንደቀራቸዉ የገለፁት ወ/ሮ ፍፁም አሰፋ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ የሚመራው የለወጥ ጉዞ ተካፋይ በመሆናቸዉ በተሰማቸውንም ታሪካዊ አጋጣሚ ጽለዉታል።  

ዩስቱስ ሊቢሽ ዩንቨርስቲ በሚባልና ፍራንክ ፈርት አቅራብያ በምትገኘዉ ጊስን ከተማ ዉስጥ የከፍተኛ ትምህርታቸዉን በማጠናቀቅ ላይ የሚገኙት አዲስ ተሽዋሚዋ ሚኒስትር ወ/ሮ ፍፁም አሰፋ ፤ የጠቅላይ ሚኒስትር አዲሱ ካቢኔ ሴቶችን በከፍተኛ ደረጃ ላይ ማስቀመጡ በኢትዮጵያ አዲስ ለዉጥ ከመሆኑም ሌላ የዓለም መገናኛ ብዙኃንን ትኩረት መሳቡንም አመልክተዋል። ከሚኒስትሯ ጋር የተደረገዉን ሙሉ ቃለ ምልልስ የድምፅ ማድመጫ ማዕቀፉን በመጫን ይከታተሉ! 

መርጋ ዮናስ

ሸዋዬ ለገሠ