1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

 «የጸጥታ ኃይላት ሁከቱን ለማስቆም የወሰዷቸው እርምጃዎች ተመጣጣኝነት ይመረመራል»ኢሰመኮ

ዓርብ፣ ሐምሌ 10 2012

የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ሃላፊ ዶክተር ዳንኤል በቀለ ለዶቼቬለ እንደተናገሩት  የጸጥታ ኃይላት በሁከቱ ወቅት የወሰዷቸውን እርምጃዎች ተመጣጣኝነት ማጣራትም ከቡድኑ ተግባራቱ አንዱ ነው።ከሁከቱና ግርግሩ ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር የዋሉ ሰዎችን ሁኔታና የእስር አያያዝም ኮሚሽኑ እንደሚከታተል አስታውቀዋል።

https://p.dw.com/p/3fV9G
Äthiopien Daniel Bekele
ምስል DW/S. Muchie

 «የጸጥታ ኃይላት ሁከቱን ለማስቆም የወሰዷቸው እርምጃዎች ተመጣጣኝነት ይጣራል»ኢሰመኮ

በኦሮምያ ክልልና በአዲስ አበባ ዙሪያ ባለፈው ሰሞን የተፈጸመውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት ዓይነትና መጠን ለመርመር  የአጥኚዎች ቡድን አቋቁሞ ወደ የአካባቢዎቹ እያሰማራ መሆኑን የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን አስታወቀ።የኮሚሽኑ ሃላፊ ዶክተር ዳንኤል በቀለ ለዶቼቬለ እንደተናገሩት  የጸጥታ ኃይላት በሁከቱ ወቅት የወሰዷቸውን እርምጃዎች ተመጣጣኝነት ማጣራትም ከቡድኑ ተግባራቱ አንዱ ነው።ከሁከቱና ግርግሩ ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር የዋሉ ሰዎችን ሁኔታና የእስር አያያዝም ኮሚሽኑ እንደሚከታተል አስታውቀዋል። የአዲስ አበባው ወኪላችን ዘገባ አዘጋጅቷል።


ሰሎሞን ሙጬ


ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ