1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ይዞታ

ሰኞ፣ መስከረም 28 2011

ኢትዮጵያ በመጪው መጋቢት ወር በሚካሄደው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብት ጉባኤ ላይ የሰብዓዊ መብት ይዞታዋ ይገመገማል። የመንግሥታቱ ድርጅት የሰብዓዊ መብት ጉባኤ በየ አራት ዓመቱ የየሃገራቱን የመብት ይዞታ በመገምገም መሻሻል ያሳዩትን ያመሰግናል፤ ያላሳዩትን ደግሞ ያወግዛል።

https://p.dw.com/p/36BR4
UN Human Rights Council Logo

9 የመብት ተቆርቋሪ ቡድኖች የግምገማ ሰነድ አዘጋጅተዋል

ኢትዮጵያም ከዚህ ቀደም በተደረጉ ሁለት ጉባኤዎች በበርካታ መብቶች በተለይም በመናገር እና በመፃፍ፤ የመሰብሰብ እና መደራጀት በመሳሰሉት መብቶች ከፍተኛ ወቀሳ ሲደርስባት ቆይቷል። ዘንድሮም ለሦስተኛ ጊዜ የምትገመገም ሲሆን ጉባኤው የወቅቱን የሀገሪቱን የሰብዓዊ መብት አያያዝ እና ባለፈው ስብሰባው እንዲሻሻሉ ከጠየቃቸው የመብት ጥሰቶች አንጻር የተደረጉ ለውጦችን እንደሚገመግም ይጠበቃል።  ዝርዝሩን ከብራስልስ ዘጋቢያችን ገበያው ንጉሤ ልኮልናል።

ገበያው ንጉሤ

ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ